ታኅሳስ 08 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ለሆቴሎች፣ ለስጋ ቤቶች፣ ለመጠጥ ቤቶች እና ለተመረጡ የንግድ ዘርፎች ለሰራተኞቻቸው ዝቅተኛ የደመወዝ ተመን ይፋ ማድረጉ ከሰሞኑ ተሰምቷል። መናኸሪያ ሬዲዮም እንደ ሀገር ዝቅተኛ የደመወዝ ተመን ባልተቀመጠት ይህ መሆኑ አግባብነት አለው ወይ ሲል የህግ እና የፋይናንስ ባለሙያዎችን ሀሳብ ጠይቋል፡፡
የህግ ባለሙያ አቶ አቤኔዘር ጥሩአየሁ፤ከሰሞኑ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ያወጣው ዝቅተኛ የደመወዝ ተመን በንግዱ ዘርፍ የተቋቋሙ ተቋማት የግብር አከፋፈላቸው በምን መልኩ መሆን እንዳለበት የሚገልፅ ነው ይላሉ። ነገር ግን ይህ አይነቱ ሁኔታ በሀገሪቱ አዲስ እና ያልተለመደ መሆኑን ገልፀው፣ቢሮው ይህ አይነቱን አሰራር ከሚከተል ይልቅ ግብር አሰባሰብ ሂደት ላይ ያላግባብ በሚጠቀሙ ተቋማት እንዲሁም ግለሰቦችን መፈተሽ የሚቻልበትን አማራጭ ተግባራዊ ማድረግ ይገባ ነበር ብለዋል፡፡
አክለውም የወጣው ዝቅተኛ የደመወዝ መጠን ለግብር ሰብሳቢው ምቹ እድልን የሚፈጥር ቢሆንም በቢሮው እና በነጋዴው ማህበረሰብ ላይ ሊፈጠሩ የሚችሉ ውጥረቶችን ታሳቢ ያደረገ አለመሆኑን ገልጸዋል፡፡ አያይዘውም በተቀመጠው አነስተኛ የደመወዝ ተመን መነሻ በማድረግ ተቋማት ሰራተኞቻቸውን እንዳይቀንሱ ስጋት አለኝ ብለዋል፡፡
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአካዉንቲንግ እና ፋይናንስ መምህር ዶ/ር ዳኪቶ አለሙ እንደሚሉት ኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት ገበያ መር የኢኮኖሚ አካሄድን የምትከተል ሀገር ሰለመሆኗ ያብራራሉ።
ነገር ግን በእነዚህ ተቋማት በኩል ዝቅተኛ የደመወዝ ተመንን ከማውጣት ይልቅ ትክክለኛ የግብር አሰባሰብ ሂደትን መከተል እንዲችሉ አማራጮችን ማስቀመጥ ይቀድማል ሲሉ ገልጸዋል፡፡
በዚህ ልክ የወጣው አዲስ አሰራር ውጤታማ ለመሆን አዳጋች ነዉ ሲሉ ገልጸዉ በተቀመጠው ዝቅተኛ የደመወዝ ተመን ምክንያት ጤናማ ያልሆኑ ውድድሮች እንዳይፈጠሩ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡
በተቋማት ላይ ዝቅተኛ የደመወዝ መጠንን ከማስቀመጥ ይልቅ በግብር አሰባሰብ ወቅት የሚታይ የግብር ስወራን መከላከል የሚቻልበትን አካሄድ መፍጠር እንደሚገባ መናኸሪያ ሬዲዮ ያነጋገራቸው ባለሙያዎች አመላክተዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ