ታኅሳስ 08 ቀን 2017 ዓ.ም(መናኸሪያ ሬዲዮ)ኢትዮጵያ እና ታንዛኒያ በተለያዩ ዘርፎች በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን ስምምነት መፈራረማቸው ተገልጿል፡፡
በስምምነቱ በሰላም እና ፀጥታ፣ ኢኮኖሚ ፣ቱሪዝም፣ ግብርና፣ ኢንቨስትመንትና ሌሎች መሰል ዘርፎች ላይ በጋራ ለመሥራት የሚያስችል መሆኑን ተገልጿል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) የሀገራቱ በቅንጅት መሥራት አልሸባብን ጨምሮ ሌሎች ሽብርተኞችን ለመከላከል ብሎም ሰላም በአኅጉሪቱ እንዲሰፍን አስቻይ ሁኔታዎችን እንደሚፈጥር በመግለጫው መናገራቸው ተመላክቷል፡፡
የታንዛኒያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የምሥራቅ አፍሪካ የትብብር ሚኒስትር አምባሳደር መሐሙድ ተሀቢት ኮምቦ በበኩላቸው በሀገራቱ መካከል ያለውን የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የቪዛ ክልከላን ማንሳት እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ