ታኅሳስ 08 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአዲስ አበባ የህግ ታራሚዎች ቀደም ብለው ይኖሩበት ከነበረው አሮጌው የቃሊቲ ማረሚያ ማዕከል አዲስ ወደተገነባው ገላን አካባቢ ወደ ሚገኘው እና በተለምዶ አባ ሳሙኤል ተብሎ በሚጠራው የቃሊቲ ማረሚያ ማዕከል ከታህሳስ 8 እስከ 13 ቀን 2017 ዓ.ም የማዘዋወር ስራ እንደሚሰራ የፌዴራል ማረሚያ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
በመሆኑም በአዲስ አበባ ቃሊቲ ማረሚያ ማዕከል ይሰጥ የነበረውን የታራሚ ቤተሰብ ጥየቃም ሆነ የቢሮ ስራ አገልግሎት ከታህሳስ 8 እስከ 13 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ተቋርጦ እንደሚቁይ አሳውቋል፡፡
በዚህም መሰረት ከዛሬ ታኅሳስ 08 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ታኅሳስ 13 ቀን 2017 ዓ.ም ደረስ የታራሚ ቤተሰብ ጥየቃም ሆነ የቢሮ አገልግሎት እንደማይኑር የፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
ከዛሬ ታህሳስ 8 ቀን 2017 .ም ጀምሮ የሚቋረጠው አገልግሎት ከታህሳስ 14 ቀን 2017 ዓ.ም ወደ መደበኛ ስራው የሚመለስ በመሆኑ አገልግሎቱ በአዲሱ የቃሊቲ ማረሚያ ማዕከል ገላን አካባቢ በተለምዶ አባ ሳሙኤል ተብሎ በሚጠራው ማዕከል ማግኘት የሚቻል መሆኑ ተመላክቷል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ