ታኅሳስ 08 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ስፔናዊው የ16 አመት የክንፍ አጥቂ መስመር ተጫዋች የሆነው ላሚን ያማል ባርሴሎና ከትላንት በስቲያ በጊዜያዊ ስቴዲየማቸው ሎስ ኮምፓኜስ በሌጋኔስ 1-0 በሆነ ጠባብ ውጤት ሽንፈት ማስተናገዳቸው አይዘነጋም።
ድሉ ለሌጋኔስ ከ2020 በኋላ የሊጉ መሪዎች ባርሴሎና ላይ የተቀናጁት መጀመሪያ ድላቸው ሆኖ መቆጠሩ ይታወቃል። የካታሎኑ ክለቡ 18ኛ ሳምንት ጨዋታቸውን ነው ያከናወኑት ነጥባቸው 38 ነው። ሁለቱ የማድሪድ ከተማ ክለቦች ገና 1 ቀሪ ጨዋታ እያላቸው አትሌቲኮ በእኩል ነጥብ ፤ ሪያል ማድሪድ ደግሞ 37 ነጥብን ይዘው ይገኛሉ። እና የሀንሲ ፍሊኩ ቡድን ከፍተኛ ጫና ውስጥ እየወደቀ ይገኛል።
ካለባቸው ጫና በላይ ነገሮችን ከባድ የሚያደርገው ወጣቱ የክንፍ አጥቂ መስመር ተጫዋች የሆነው ላሚን ያማል በዚ ጨዋታ ላይ የቁርጭምጭሚት ጉዳት ማስተናገዱ ተገልጿል። ይህም አነሰ ከተባለ ለ1 ወር ከሜዳ እንደሚርቅ እየተገለፀ ይገኛል።
ያማል ተመሳሳይ ጉዳት ሲያጋጥመው ለመጀመሪያ ጊዜ አይደለም። ባሳለፍነው ህዳር ወር መጀመሪያ ሳምንት በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ወደ ሰርቢያ አቅንተው ከሬድ ስታር ቤልግሬድ ጋር ባደረጉት ጨዋታ ተጫዋቹ ቀኝ እግሩ ላይ grade 1 syndesmosis ወይም የቁርጭምጭሚት ጉዳት አጋጥሞት እስከ 3 ሳምንት ከሜዳ ርቆ እንደነበር አይዘነጋም።
በእነዚህ ጊዜያት ከሪያል ሶሲዳድ ፤ ሌጋኔስ እና በሻምፒዮንስ ሊጉ ከብሬስት ጋር ባደረጉት ጨዋታ ላይ አልተሰለፈም። ከትላንት በስቲያ በነበረው ጨዋታ ከኒዩ ከተባለው ተጫዋች ጋር የነበረው ግጭት ያማል ምቾት ተሰምቶት እንዳይጫወት አድርጓታል። በጨዋታው ላይ ምንም እምኳ እስከ 74ኛው ደቂቃ ላይ ድረስ ሜዳ ላይ ቢቆይም በመጀመሪያው አጋማሽ ብቻ ሁለት ጊዜ ለመቀየር ጥያቄ አቅርቦ እንደነበር አይዘነጋም።
የካታሎኑ ክለብ የፍራንኪ ዲዮንግ የቁርጭምጭሚት ጉዳት ተጫዋቹን ቢያንስ ለ1 አመት ከሜዳ አረሰቆት እንደነበር አይዘነጋም።
ስለዚህ ላሚን ያማል ላይ ተደጋጋሚ የቁርጭምጭሚት ጉዳት መፈጠሩ ተጫዋቹ ይበልጥ የጉዳት ጊዜውን እንዳያራዝምበት የሚያሰጋቸው በመሆኑ ከ1 ወር በኋላም ለተወሰነ ጊዜ ያማል እረፍት ወስዶ እንዲመጣ ሊወስኑ ይችላሉ ተብሏል።
ስለዚህ ሊሚን ያማል በቀጣይ ባርሴሎና ከተከታያቸው አትሌቲኮ ማድሪድ ጋር የሚያደርጉት እጅግ ተጠባቂው የላሊጋ ጨዋታ ፤ በኮፓ ዴል ሬው ከባርባስትሮ ከተሰኘው ክለብ ጋር እንዲሁም ከአትሌቲኮ ቢልባኦ ጋር የሚያደርጉት የስፔን ሱፐር ካፕ ጨዋታ ላይ ያማል የመሰለፍ እድሉ ጠባብ ነው ተብሏል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ