ታኅሳስ 04 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ፈረንሳዊው ኮኮብ ኪሊያን ምባፔ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የምድብ 6ኛ ጨዋታ ጣልያን ቤርጋሞ ላይ ሪያል ማድሪድ አታላንታን 3-2 ባሸነፉበት ጨዋታ ላይ 35ኛው ደቂቃ ላይ የጭን ጉዳት በማስተናገዱ ምክንያት ከሜዳ ተቀይሮ ለመውጣት መገደዱ አይዘነጋም።
አሰልጣኝ ካርሎ ተጫዋቹ ጉዳቱ ቀለል ያለ ነው ብሎኛል ብለው ተናግረው እንደነበር አይዘነጋም። ታዲያ አሁን ምርመራውን ካከናወነ በኋላ የተወሰነ እረፍት ብቻ እንደሚፈልግ እና 2 ሳምንት በማይሞላ ጊዜ ውስጥ ወደ ሜዳ እንደሚመለስ ተገልጿል።
ይህ ማለት ኪሊያን ምባፔ በላሊጋው ነገ ከራዮ ቫይካኖ ጋር እንዲሁም ለፊፋ ኢንተርኮንቲኔንታል ካፕ ውድድር ከሜክሲኮአዊው ተወካይ ፓቹካ ወይም ከግብፁ አል አህሊ ጋር በኳታር ዶሀ በሚደረገው ጨዋታም ተጫዋቹ የመሰለፊ ጉዳይ አጠራጣሪ ነው ተብሏል።
ሎስ ብላንኮሶቹ አቻኩለው ወደ ሜዳ እንዲመለስ ያደርጉታል ተብሎ አይገመትም። ፈረንሳዊው ኮኮብ ኪሊያን ምባፔ ወደ ማድሪድ ካቀና በኋላ ትችቶችን ቢያስተናግድም የቡድን አጋሮቹ ግን የዋንጫ ክብሮችን እንድናሳካ ይረዳናል በሚል ከጎኑ መሆናቸውን ሲያሳዩት ቆይተዋል። በአጠቃላይ ኪሊያን ምባፔ በነጩ ማልያ ባደረጋቸው 22 ጨዋታዎች 12 ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ