ታኅሳስ 04 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የከተማ መሰረተ ልማት እና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ እሸቱ ተመስገን(ዶ/ር) እንደ ሀገር የመሬት ሚኒስቴር መቋቋም እንዳለበት ምክረ ሃሳብ አቅረበዋል፡፡
በከተማ የመሬት ይዞታና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ አዋጅ እንዲሁም የከተማ መሬትን በሊዝ ስለመያዝ በወጣው ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ቋሚ ኮሚቴው ውይይት ያደረገ ሲሆን፤ ከአባላቱ በኩል ለተነሱ ጥያቄዎች የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
በዚህ ወቅት የከተማ መስረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ እሸቱ ተመስገን(ዶ/ር) እንደ ሀገር መሬት ትልቁ ሀብት በመሆኑ እራሱን በቻለ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት መመራት እንደሚገባው ተናግረዋል፡፡
የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ፋንታ ደጀኔ በበኩላቸው፤ አዲሱ ረቂቅ አዋጅ በርካታ ማሻሻያዎችን በውስጡ የያዘና አሁን ላይ በፍጥነት እያደገ ለሚገኘው የክትመት ምጣኔ ምላሽ የሚሰጥ መሆኑን አብራረተዋል፡፡
በተለይም የመሬት ምዝገባ ላይ ያለውን የተንዛዛ አሰራር ከስር መሰረቱ የሚቀይር መሆኑን አብራርተዋል፡፡
ረቂቅ አዋጁ በቀጣይ በምክር ቤቱ በኩል የተሰጡ ግብዓቶች ተካውበት ይጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተመላክቷል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ