ታኅሳስ 04 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ጥቁሩ ፈርጥ ባሳለፍነው እሮብ በነበረው የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የ6ኛ ዙር ጨዋታ ሞኒኮ ላይ 2 ጎል አስቆጥሮ 1 ኳስ አመቻችቶ ማቀበሉ እና የጨዋታው ኮኮብ ተብሎ መመረጡ አይዘነጋም።
እንግሊዛዊው ኮኮብ ለአርሰናል እጅግ በጣም ቁልፍ ሚናን የሚወጣ ተጫዋች ነው። አንድ ፤ ለአንድ በሊጉ እጅግ አደገኛ የሚባል ተጫዋች ነው። ከሁሉም በተጨማሪ ለሰሜን ለንደኑ ክለብ የጎል መንስኤ ፤ እና ወጥነት ባለው መልኩ ግልጋሎት ከሚሰጡ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ነው።
በሻምፒዮንስ ሊግ በተሳተፈባቸው 14 ጨዋታዎች 14 የጎል ተሳትፎዎች አሉት። በፕሪሚየር ሊጉ በርካታ ኳሶችን አመቻችቶ በማቀበል ሳካ እየመራ ይገኛል። በአጠቃላይ ዘንድሮ ባደረጋቸው 21 ጨዋታዎች 12 ጎል ሲያስቆጥር 9 ኳስ አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።
በክለቦች ትልቁ የውድድር መድረክ ላይ በዚህ ሳምንት አስደናቂ እንቅስቃሴን ካሳዩ ተጫዋቾች መካከል በዋናነት ሳካ አንዱ ስለነበር የሻምፒዮንስ ሊግ የሳምንቱ ምርጥ ተጫዋች ተብሎ መሰየሙን ለማወቅ ተችሏል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ