ታኅሳስ 04 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የንግድ ውድድሩን ተከትሎ የጤና ተቋማት አማላይ ማስታወቂያዎችን በማስነገር ህብረተሰቡን ወደ ተሳሳተ እይታ እየመሩት ነው ያለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብና መድሃኒት ባለስልጣን ነው፡፡
መናኸሪያ ሬዲዮ ያነጋገራቸው የተቋሙ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ እንጋ እርቃታ፤ በህክምናው ዘርፍ የባህል እና ዘመናዊ ህክምናዎች በስፋት መኖራቸውን ገልጸው፤ በህክምና ሂደት እየታዩ ያሉ ክፍተቶች ሰፊ በመሆናቸው ዘርፉን አሳሳቢ አድርጓል ብለዋል፡፡
በመገናኛ ብዙሃን እና በተለያዩ አማራጮች የሚተላለፉ ማስታወቂያዎች ትክክለኛ ይዘት ያላቸው እንዲሁም የወጡ ህጎች እና ደንቦችን በጠበቀ መልኩ መሆን ቢገባቸውም ህግ እና ደንቡን በተላለፈ መልኩ ማስታወቂያ የሚያስነግሩ ተቋማት መኖራቸውን ገልጸዋል፡፡
አክለውም በመገናኛ ብዙሃኑ በሚሰራጩ ማስታወቂያዎች አማካኝነት ህብረተሰቡ ለከፋ የስነ-ልቦና ጫና እንዳይጋለጥ፤ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የክትትል እና ቁጥጥር ስራ ይሰራል ብለዋል፡፡
የጤና ተቋማትም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከሰጣቸው የሙያ ማረጋገጫ ደረጃ በላይ አገልግሎት እንደሚሰጡ የማስተዋወቅ ችግር እንደሚስተዋልባቸው ተናግረዋል፡፡
በተለይም በከተማዋ በጥርስ ህክምና እና በጸጉር ንቅለ ተከላ ዘርፍ የተሰማሩ ተቋማት በመገናኛ ብዙሃኑ በኩል እያስተላለፋቸው ያሉ ማስታወቂያዎች እጅግ አማላይ እና የተጋነኑ በመሆናቸው እርምጃ እየተወሰደባቸው ነው ብለዋል፡፡
የጥፋት ደረጃቸው ከፍተኛ የሆኑ ተቋማትን ፍቃድ የመንጠቅ እርምጃ እንደሚወሰድም አስታውቀዋል፡፡
በዘመናዊም ይሁን በባህላዊ መንገድ ህክምና የሚሰጡ የጤና ተቋማት የተጋነነ ማስታወቂያ እያስነገሩ መሆኑን ተከትሎ፤ ከፍተኛ ግነት ያለባቸው ማስታወቂያዎችን መቆጣጠር እንዲቻል የአዋጅ ማሻሻያ ሊደረግበት እንደሚገባም ነው የገለጹት፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ