መንግሥት በየደረጃው የሚገኘውን መዋቅር በመፈተሽ፣ በሙስና ወንጀል የሚሳተፉ አመራሮችንና ሌሎች ተዋንያንን ለሕግ በማቅረብ ለሙስና ምቹ ሁኔታ እንዳይፈጠር ጥረት እያደረገ መሆኑ ይታወቃል።
በጥናት በተደረሰባቸው የመንግሥት ሹመኞች፣ የመንግስት ተቋማት ሰራተኞች፣ አቀባባዮችና ጉቦ ሰጪዎች ላይ ምርመራ እያደረገም ይገኛል፡፡
ከለውጡ በፊት በ20 ዓመታት ውስጥ በህገ- ወጥ መንገድ ከሃገር የወጣው ገንዘብ 30 ቢሊዮን የአሜርካ ዶላር ሊሆን እደሚችል ተጠቁሟል። ይህ ገንዘብ ለ100 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን በነፍስ ወከፍ ቢከፋፈል እንኳን እያንዳንዱ ከ7 ሺ 200 ብር ያላነሰ ገንዘብ ይደርሰው ነበር።
ይህ ሙስና ዛሬም ለኢትዮጵያ የደህንነት ስጋት ሆኖ መቀጠሉን እውን ነው። ኢትዮጵያውያን በተለያዩ እምነት ዘርፎች ስር ጥብቅ ሃይማኖታዊ ትስስር እንዳላቸው ይነገራል። ይህም በተለያዩ የዕለት ከዕለት ሕይወታቸው ውስጥ በጉልህ የሚታይ ነው። ከጊዜ ወደ ጊዜ ግን የሃይማኖት ተቋማትም በሙስናው ላይ ስማቸው ሲነሳ ይስተዋላል የዛሬው የዳሰሳ ጥንቅራችንም በሃይማኖት ተቋማት በሚፈፀሙ የሙስና ተግባራት ላይ ትኩረቱን አድርጓል :- ማህሌት ሙሉጌታ
ምላሽ ይስጡ