ታኅሳስ 03 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በሰሜን ምስራቅ፣ በምስራቅ፣ በመካከለኛዉና በደቡብ ደጋማ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የሌሊትና የማለዳዉ ቅዝቃዜ በአንጻራዊ ሁኔታ የሚጠናከር በመሆኑ በቋሚ ተክሎች፣ በጓሮ አትክልቶችና በመስኖ በሚለሙ ሰብሎች እድገት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚኖረው የግብርና ሚኒስቴር ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል፡፡
በሚቀጥሉት አስር ቀናት አብዛኛዎቹ ተፋሰሶች ደረቅ ሆነው እንደሚቆዩ የሚጠበቅ ቢሆንም በጥቂት ተፋሰሶች ላይ መጠነኛ እርጥበት እንደሚገኝም ተጠቁሟል፡፡ መጠነኛ እርጥበት ከሚጠበቅባቸው ተፋሰሶች መካከል ባሮ አኮቦ፣ በመካከለኛ እና ታችኛው ኦሞ ጊቤና ስምጥ ሸለቆ ተፋሰሶች ናቸው፡፡
በሌላ በኩል በአብዛኛው አባይ፣ ተከዜ፣ አዋሽ፣ አይሻ፣ አፋር ደናክል፣ ኦጋዴን እንዲሁም መረብ ጋሽ ተፋሰሶች ደረቅ ሆነው የሚቆዩ ሲሆን፤ በተፋሰሶቹ የሚገኘውን የውሃ ብክነትን በመቀነሰ በአግባብ ጥቅም ላይ ማዋል እንደሚያስፈልግ ሚኒንስቴር መስሪያቤቱ ለጣቢያችን በላከልን ጥናት አመላክቷል፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘም የበጋው ደረቅ፣ ፀሐያማና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ በአብዛኛዎቹ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የሚስተዋል እና የሌሊትና የማለዳዉ ቅዝቃዜ በተለይም በሰሜን ምስራቅ፣ በሰሜን፣ በምስራቅና በደቡብ ደጋማ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ቀጣይነት ይኖረዋል ብሏል፡፡
በደቡብና ደቡብ ምዕራብ የሃገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ክምችት የሚኖር ሲሆን በተለይም በደቡብ ምዕራብና በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የሀገራችን ክፍሎች ሶማሌ ክልል ደቡባዊ ክፍል፤ የጉጂ የቦረና ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል፤ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዞኖች ላይ አልፎ አልፎ በሚኖሩት ቀናት አነስተኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖርም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለጣቢያችን በላከው መረጃ አመላክቷል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ