ታኅሳስ 02 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ከቅመማ ቅመም ምርት የወጪ ንግድ ለማግኘት ከታቀደው እቅድ ከ75 በመቶ በላይ ማሳካት እንደታቻለ የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለስልጣን ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል፡፡
በ4 ወራት ውስጥ 6 ሺህ 558 ነጥብ 6 ቶን ቅመማ ቅመም ለውጭ ገበያ ማቅረብ መቻሉን የተናገሩት የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሻፊ ዑመር ከዚህም ከ3 ሚሊዮን 100ሺህ ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል ብለዋል፡፡
በኢትዮጵያ ከ50 በላይ ቅመማ ቅመሞች እንደሚመረቱ የገለጹት ዳይሬክተሩ፤ ከእነዚህ ውስጥም 16ቱ ለዓለም ገበያ እንደሚቀርቡ ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ ከምርቶቹ ተጠቃሚ እንዲትሆን ዝቅተኛ የመሸጫ ዋጋ ተመን ለማውጣት ከብሄራዊ ባንክ ጋር እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ኮረሪማ፣ እርድ፣ ጥምዝ፣ ቁንዶ በርበሬ እና በርበሬ ተጠቃሽ ቅመሞች መሆናቸውን የገለጹት የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር፤ የሽያጩ ውጤት ካለፈው አመት ጋር ሲነፃፀር ከ90 በመቶ በላይ የሚሆን ልዩነት እንዳለው ጠቁመዋል፡፡
በኢትዮጵያ የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ብቻ የሻይ ምርትን ለውጭ ገበያ የማቅረብ ስራ እንደሚሰራ የተናገሩት አቶ ሻፊ፤ ባለፈው አራት ወር ውስጥ የተገኘው ገቢ አነስተኛ መሆኑን አብራርተዋል፡፡ ኢትዮጵያ ለሻይ ምርት ምቹ የአየር ፀባይና አፈር ያላት ሃገር በመሆኗ አርሶ አደሩና ባለሃብቱ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ምርቱን ማስፋፋት ይገባቸዋል ብለዋል።
ምርቶች በህገ ወጥ መንገድ ከሃገር እንዳይወጡ በእያንዳንዱ ድንበር ላይ ከተለያዩ የሕግ አካላትና የጉምሩክ ሠራተኞች ጋር በመተባበር ሕገ-ወጦችን ለመያዝ በጥብቅ ቁጥጥር እየተሰራ መሆኑንም የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሻፊ ኡመር አመላክተዋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ