ታኅሳስ 02 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የሀገሪቱ ሕገ-መንግስታዊ ፍርድ ቤት የ68 ዓመቱ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ሕግ የሚፈቅድላቸውን ሁለት የስልጣን ዘመን አገልግለው የጨረሱ በመሆናቸው እንዳገዳቸው አስታውቋል፡፡ ይሁንና በአውሮፓውያኑ 2015 ለመጀመሪያ ጊዜ የፕሬዝዳንትነቱን መንበረ ስልጣን የተቆናጠጡት ሉንጉ በስልጣን ላይ እያሉ ሕይወታቸው ያለፈውን ሚካኤል ሳታ ተክተው ለ20 ወራት ብቻ ያገለገሉበት በመሆኑ ቁጥር ውስጥ እንደማይገባ እየተከራከሩ ነው፡፡
በዛምቢያ አንድ ፕሬዝዳንታዊ የስልጣን ዘመን ለአምስት ዓመታት የሚዘልቅ ሲሆን ኤድጋር ሉንጉ ከሶስት ዓመታት በፊት በተደረገው ምርጫ በፍርድ ቤት ተፈቅዶላቸው መወዳደር ችለው ነበር፡፡ የዛምቢያ መንግስትም ወደ ፖለቲካ ለመመለስ መወሰናቸውን ተከትሎ ከጡረታ መብታቸውና ጥቅሞቻቸው አግዷቸው ቆይቷል፡፡
በምርጫው በአሁኑ ፕሬዝዳንት ሀካይንዴ ሒቺሌማ መሸነፋቸው ይታወሳል፡፡ ባለፈው ወር “የቶንሴ ሕብረት” የተሰኘው የሀገሪቱ መንግስት ተቃዋሚ ፓርቲ ሉንጉ በ2026 ምርጫ እንዲወክሉት መርጧቸው ነበር፡፡ በስልጣን ላይ ያሉት ሒቺሌማ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዳግም እንዲወዳደሩ የፈቀዱትን ሦስት ዳኞች ከኃላፊነታቸው ማንሳታቸውን የቢቢሲ ዘገባ አስታውሷል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ