ታኅሳስ 02 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የሕዝብና የጭነት አጓጓዞች በሆኑ ተሽከርካሪዎች በየከተማው የሚሰበሰቡ የኮቴ ክፍያዎች ሕጋዊነት የሌላቸዉ መሆኑንና የብዝበዛ ድርጊት እየተፈፀመ እንደሆነ የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር ለመናኸሪያ ሬዲዮ ገልጿል።
በሀገሪቱ ባሉ ኬላዎች የሚፈጸሙ የኮቴ ክፍያዎች ላይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እውቅና ያልሰጠውና አግባብነት በጎደለው መልኩ በሕጋዊ ሽፋን የሚደረጉ መሆናቸውን የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር የአገልግሎትና ቁጥጥር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ በርዖ ሁሴን ተናግረዋል።
በተጨማሪም እንዲህ አይነት ሕገ-ወጥ ክፍያ የፈጸሙ ኬላዎች መብዛታቸው በሀገር ኢኮኖሚ የሚያሳድረው ተጽዕኖ ከፍተኛ እንደሆነና በተለይም ደግሞ የጉዞ ላይ መንገላታትን እየጨመረ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ገቢ ማሰባሰብ በሚል በሕጋዊ ሽፋን የሚካሄዱ ምዝበራዎች የትራንስፖርት ሴክተሩ ላይ ለሚሳተፉ አካላት እንቅፋት እንደሆኑም ሚኒስትር ዴኤታው ገልጸዋል።
ምንም እንኳን ሕገ-ወጥ ክፍያ የሚያስከፍሉ አካላት በርካቶች ቢሆኑም በአንዳንድ የሀገሪቱ ክፍል የሚገኙ ኬላዎች ኃላፊነታቸውን እንደሚወጡ ገልጸው በሕገ-ወጥ የገቢ ማሰባሰብ ላይ የተሰማሩ ኬላዎችን በሕግና አሰራር መሰረት ከስራቸው ለማስቆም እንደ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት እየተሰራ መሆኑን የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር የአገልግሎትና ቁጥጥር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ በርዖ ሁሴን ለጣቢያችን አመላክተዋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ