ታኅሳስ 02 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በመቀለ ከተማ አጠቃላይ የአደባባይ ሰልፍ እንዳይደረግ የሚል ክልከላ ወጥቷል መባሉን ተከትሎ መናኸሪያ ሬዲዮ ስለ ጉዳዩ አጣርቷል።
የትንሳኤ ሰባ-አንደርታ ፓርቲ ሊቀ መንበር አቶ ከበደ አሰፋ በመቀለ ዙሪያ በጊዜያዊ አስተዳደሩ በግልፅ ያልተቀመጠ እና ህጋዊ ያልሆነ የድጋፍም ሆነ የተቃውሞ ሰልፍ ክልከላ መደረጉን ገልጸዋል፡፡
ለአደባባይ ሰልፎች በጊዜያዊነት ክልከላ ያወጣው የክልሉ የፀጥታ ግብረ ሃይል የተባለው አካል መሆኑን የገለጸው ፓርቲው፤ ይሁን እንጅ ትክክለኛ የህግ ማዕቀፍ የሌለውና ተገቢ ያልሆነ ውሳኔ ነው ብሏል።
የትግራይ ክልል ፅህፈት ቤት ቢሮ ምክትል ሃላፊ እና የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሃላፊ ዶክተር ገብሩ ካህሳይ በበኩላቸው፤ “በመንግስት ደረጃ በግልፅ በሰነድ የተቀመጠ ክልከላ የለም፣ አሁን ላይ በክልሉ የተለየ የተፈጠረ ሰላምን የሚያውክ የፀጥታ ችግርም አይታይም” ብለዋል፡፡
ምናልባትም ክልሉ ከዚህ በፊት የነበረበት የጦርነት ሁኔታን በማሰብ ህብረተሰቡ በስጋት የፈጠረው አሉባልታ ይሆናል ሲሉም ተናግረዋል። ከፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት በኋላ በክልሉ የተጣለ የሰላማዊ ሰልፍ ክልከላ እንደሌለና ነዋሪው የአደባባይ ሰልፍ የማድረግ ህገ መንግስታዊ መብቱ የተጠበቀ መሆኑን አመላክተዋል።
የጽሕፈት ቤት የኮሙኒኬሽን ኃላፊው በክልሉ አደባባይ የመውጣት እና ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብት አልተገደበም ቢሉም፤ ጣቢያችን ያነጋገራቸው በክልሉ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ግን የአደባባይ ሰልፎች መታገዳቸውን ነው የገለጹት።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ