ታኅሳስ 02 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የሪል እስቴት ዘርፉ ዋጋ መወደድ ዜጎች የቤት ባለቤት የመሆን እድላቸውን እንዳመናመነው ይገለጻል፡፡ በዚህ ሒደት ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ቀዳሚ ተጠያቂ ሊሆኑ እንደሚገባ ለመናኸሪያ ሬዲዮ ሃሳባቸውን ያሳፈሩ የህግ ባለሙያዎች ተናግረዋል፡፡
በዘርፉ ለሚስተዋሉት ችግሮች በቀዳሚነት አልሚዎች እና ደላሎች ተጠያቂ ቢሆኑም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መገናኛ ብዙሃን እና ጋዜጠኞች ለችግሩ መስፋፋት ተጠያቂ ሊሆኑ እንደሚገባ ጠበቃና አለም አቀፍ የህግ ባለሙያ አቶ ጥጋቡ ደሳለኝ ገልፀዋል፡፡
ያልተገነባ ቤትን በማስተዋወቅ ሰዎች እንዲገዙና እንዲከስሩ ከማድረግ አንጻር መገናኛ ብዙሃኑ ሚናቸው ከፍተኛ መሆኑን ነው የህግ ባለሙያው የሚናገሩት፡፡
በባንክ ስራ ፍቃድ አዋጅ 591/2000 አንቀፅ 17 ላይ እንደተደነገገው ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ማንኛውም ግብይት በልዩ ሁኔታ ካልተፈቀደ በስተቀር በኢትዮጵያ ብር ብቻ እንዲገበያይ እንደሚያዝ የህግ ባለሙያው ጠቅሰው፤ በሪል እስቴት ዘርፉ ላይ በቀዳሚነት ከሚነሱ ክፍተቶች ውስጥ ክፍያቸው በውጭ ምንዛሬ መሆኑ ሌላኛው ችግር ነው ብለዋል፡፡
ከሰሞኑን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፀደቀው የሪል እስቴት ዘርፍን የሚመለከት ረቂቅ አዋጅ የመገናኛ ብዙሃን ተጠያቂነትን በግልፅ እንዳላስቀመጠ የሚገልጹት ሌላኛው በማንኛውም የፌደራል ፍርድ ቤቶች ጠበቃና የህግ አማካሪ አቶ ዳንኤል ፍቃዱ በዘርፉ ላይ የሚኖረው ተጠያቂነት በግልፅ ሊቀመጥ ይገባል ብለዋል፡፡
አብዛኛው የሪል እስቴት ማስታወቂያዎች በወኪሎች የሚሰሩ በመሆኑ እነሱንም አዋጁ ተጠያቂ ማድረግ እንደነበረበት የህግ ባለሙያው ጠቁመዋል፡፡
ሪል እስቴቶች ከ80 በመቶ በላይ ግንባታቸው ካልተጠናቀቁ ለሽያጭ እንደማይቀርቡ የሚደነግግ ረቂቅ አዋጅ ከሰሞኑን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መጽደቁ ይታወሳል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ