ታኅሳስ 02 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የኢፌድሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አስቀስላሴ 21ኛው የአለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በሚከበርበት መድረክ የክብር እንግዳ ሆነው በተገኙበት መድረክ ሙስናን ለመከላከል ከተሰራው ይልቅ የተነገረው ያይላል ብለዋል።
በየዓመቱ የሙስና ቀንን ከማክበርና በንግግር ከመግለጽ በዘለለ በርካታ ቁርጠኛ የሆኑ አሰራሮችና ውጤታማ አፈጻጸም ያስፈልጋል ሲሉም ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል።
በተለይም እንደ ሀገር ተቋማዊ የሆነ አሰራር ማበጀት በጣም አሰፈላጊ መሆኑንም ተናግረዋል።
እንደ ሀገር መሰረታዊ የመፍትሄ አካል መሆን አለባቸው ያሏቸውን ተቋማትም ፕሬዝዳንቱ የገለጹ ሲሆን የትምህርት ስርዓቱ የሞራልና የስብዕና ስራ ላይ በእጅጉ መስራት እንዳለበት፣ቤተሰብና የሃይማኖት ተቋማትም መልካም እሴቶችን በማጎልበት ረገድ ሚናቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።
የመገናኛ ብዙሃኑም ከተጠቀሱት እኩል ከፍ ያለ ሚና መውሰድ እንዳለባቸው ፕሬዝዳንቱ አመላክተዋል።
21ኛው ዓለም አቀፍ የፀረ ሙስና ቀን “ወጣቶችን ያማከለ የፀረ ሙስና ትግል፣ የነገን ስብዕና ይገነባል” በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ እየተከበረ ይገኛል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ