ታኅሳስ 02 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በሮበስት ቢዝነስ ግሩፕ እና በሰላሳ መልቲ ሚዲያ አዘጋጅነት፣ ለ24 ቀናት የሚቆይ ሀገር አቀፍ ኤክስፖ ከንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በኤግዚቢሽን ማዕከል እና መስቀል አደባባይ ይካሄዳል ተብሏል።
በቀጣይ አርብ ታህሳስ 4 ቀን 2017 ዓ/ም የሚከፈተው እና እስከ ገና ዋዜማ የሚቆየው ኤክስፖ፣ የሀገር ውስጥ አምራቾችን፣ አስመጪና ላኪዎችን፣ የሪል እስቴት እና የመኪና አቅራቢ ድርጅቶችን ጨምሮ ከ500 በላይ ነጋዴዎች እንዲሁም ከአምስት የውጭ አገራት የሚመጡ ተሳታፊዎች የተዘጋጀ መሆኑን የቴሌብር የአዲስ ገና 2017 ኤክስፖ አዘጋጅ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሳምሶን ሽፈራው ተናግረዋል።
በዓልን ተከትሎ ሊያጋጥም የሚችለውን የምርት እጥረት እና የዋጋ ንረት ለመቀነስ፣ እንዲሁም ዜጎች በአንድ አካባቢ ሁሉንም አገልግሎት እንዲያገኙ እና የጋራ ትርፋማነትን ለማሳደግ በማሰብ በከፍተኛ ወጪና ቅድመ ዝግጅት የተዘጋጀ መሆኑንም ተናግረዋል።
በኤክስፖው ትልቁ የገና ዛፍ በመስቀል አደባባይ እየተሰራ መሆኑን እና 2017 የቡና ሲኒዎችን የሚይዝ ረከቦትም እየተዘጋጀ እንዳለ ተገልጻል፡፡
በኤክስፖው 100 ድምፃውያን እና አምስት ባንዶች እንዲሁም ሌሎች የኪነጥበብ ባለሙያዎች እንደሚገኙበት በመግለጫው ተጠቅሷል።
የዘንድሮው የገና ኤክስፖ ለተሳታፊዎች በተዘጋጀ የዕድል ዕጣ የቤት ሽልማት እንደሚኖርም ተገልጿል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ