ታህሳስ 01 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በጋምቤላ ክልል የወባ በሽታ ምርመራ ከሚያደርጉ ከሀምሳ በላይ ሰዎች በበሽታው የተያዙ መሆናቸውን የክልሉ ጤና ቢሮ ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል፡፡
የጋምቤላ ጤና ቢሮ የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር የወባ ፕሮግራም ባለሙያ አቶ አዲሱ ጦና፤በክልሉ ከፍተኛ የወባ በሽታ ስርጭት መኖሩን በመግለፅ በወረርሽኙ የሚያዙ ሰዎች በሳምንት እስከ አራት ሺሕ ይደርሳሉ ብለዋል፡፡
ቢሮው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ በመሆን በሽታውን ለመቆጣጠር እየሰራ መሆኑን የገለፁት ባለሙያው፤ በቀጣይ ሳምንት እስከ ታች ለሚገኙ አመራሮች የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ ይጀመራል ሲሉም ገልጸዋል፡፡ የአጎበር ስርጭት እየተደረገ ቢሆንም ክፍተቶች እንደሚስተዋሉ አንስተዋል፡፡
አክለዉም በክልሉ በሚገኙ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ስርጭቱ መጨመሩን አቶ አዲሱ ተናግረዋል፡፡
በጋምቤላ ክልል የወባ ስርጭትን ለመቆጣጠር ቤት ለቤት ማህበረሰቡን የማስተማር ስራዎች ቢሰሩም ለውጥ አለማምጣቱን አመላክተዋል፡፡ በኢትዮጵያ በመቶ ሺሕዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በወባ በሽታ መያዛቸውን መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ