ኅዳር 30 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ማንቸስተር ዩናይትድ በስፖርቲንግ ዳይሬክተርነት ሚና እና ሀላፊነት ላይ የሾሙትን ግለሰብ ዳን አሽወርዝን ከሚናው ማሰናበታቸው ተሰምቷል።
ቀያዮቹ ሰይጣኖች በIneos chemical group ስር በዚህ ድርጅት የ1/4ኛ ድርሻ ባለቤትነት ስር ከወደቁ በኋላ 2 የዝውውር መስኮት አሳልፏል።
የineos chemical groupኡ ቴክኒካል ዳይሬክተር በሆነው ሰር ዴቭ ብሬይልስፈርድ የሚመራው የክለቡ መሰረታዊ የሚባለው የእግርኳስ ኦፕሬሽን በዋናነት የአንድ ክለብ የጀርባ አጥንት እየተባለ የሚጠራው የቴክኒካል ዳይሬክተርነት ሚና ላይ አንድ ግለሰብ በመሾም የዝውውር መስኮቱን እንዲመራላቸው በማሰብ ስማቸው በተደጋጋሚ ከቀድሞው የኒውካስሉ ቴክኑካል ዳይሬክተር ዳን አሽወርዝ ጋር ሲያያዝ መቆየቱ የሚታወስ ነው። የተወሰኑ ጊዜዮችን ከፈጀ ድርድር በኋላ ይሄንን ግለሰብ በፈረንጆቹ ባሳለፍነው ሰኔ 1 ላይ መሾሙ አይዘነጋም።
ማንቸስተር ዩናይትድ ሜዳ ላይ ለሚዪሳየው የተጪዋቾች የእግርኳስ እንቅስቃሴ እንዲሁም ምልመላዎች እና የተጫዋች ዝውውር ሲከናወን አሽወርዝ ከፍተኛ ሚና እና ሀላፊነት እንዳለበት የሚታወቅ ነው።
ታዲያ ክለቡ በነዚህ ጉዳዮች ላይ እያሳየ በሚገኘው ነገር ደስተኛ አልነበረም። The athletic እንደዘገበው ከሆነ ዩናይትድ ቅዳሜ ምሽት በሜዳቸው ኦልድትራፎርድ በኖቲንጋም ፎረስት ያጋጠማቸውን ሽንፈት ተከትሎ የክለቡ ስራ አስኪያጅ ኦማር ቤራዳ ቢሮ የ53 አመቱ ግለሰብ ቢሮአቸው እንዲገኝ ቀጭን ትዕዛዝ ስለማስተላለፋቸው ከዛም ስንብቱ ስለመሰማቱ ዘግቧል።
አሽወርዝ የዩናይትድ የክረምቱ የ200 ሚሊዮን ፓውንዲ ግዢዎች ላይ እጀለ አለበት። ክለቡ ደግሞ የተሸመቱት ተጫዋቾች ሜዳ ላይ አመርቂ እና አጥጋቢ እንቅስቃሴን እያሳዩ አይደለም የሚገኙት በሚል ነው ስንብታቸው የተሰማው።
በአሁን ሰአት አለማችን ላይ ከሚገኙ ትልቅ ስም ካላቸው ስፖርቲንግ ዳይሬክተሮች መካከል አንዱ ነው። እና የineos chemical group ግለሰቡኝ ለማምጣት በጣረው ልክ ለማሰናበትም የቸኮለበት መንገድ ርዕሰ ጉዳዩን መነጋገሪያ እያደረገው ይገኛል።
ዳን አሽወርዝ በ2022 የካቲት ወር ላይ ነበር ብራይተንን ለቆ ኒውካስልኝ የተቀላቀለው በሁለቱ ክለቦች በነበረው የስራ ዘርፍ በሊጉ አስደናቂ ጊዜን እንዲያሳልፉ ምክንያት የሆኑትን ዋና ተዋናዮቹን ማለትም በርካታ ቁልፍ የሚባሉ ተጫዋቾች በማስፈረም ጥሩ ተቀባይነት እና ትልቅ ስም ማትረፉ አይዘነጋም።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ