ኅዳር 30 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የወሎ ተሪሸሪ ኬር ሕክምናና የማስተማሪያ ሆስፒታል ግንባታ ፕሮጀከት ፅ/ቤት እና በወሎ ተሪሸሪ ኬር ሕክምናና የማስተማሪያ ሆስፒታል ግንባታ ፕሮጀክትን በ2015/ 2016 በጀት ዓመት የተከናወነ ክዋኔ ኦዲት ሪፖርትን መነሻ በማድረግ የፌዴራል ዋና ኦዲተር ሆስፒታሉ 23.7 ሚሊዮን ብር ለባንክ ገቢ አለማድረጉን ለምክር ቤቱ አስታውቋል፡፡
የወሎ ተሪሸሪ ኬር ሕክምናና የማስተማሪያ ሆስፒታል ግንባታ ፕሮጀክትን ለማቀላጠፍ ከመንግስት በሚበጀት በጀት እና ከህዝቡ በሚገኝ ገቢ ግንባታ ለማከናወን ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ እንቅስቃሴዎች እንደነበሩ የሚናገሩት የፌዴራል ዋና ኦዲተር ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ 16 ሚሊዮን 43ሺህ 63 ብር ከ19 ሳንቲም ከኩፖን ሽያጭ ፤ ከቶንቦላ ሽያጭ 7.7 ሚሊዮን ብር በድምሩ 23.7 ሚሊዮን ብር ወደ ባንክ ገቢ አለመደረጉን ዋና ኦዲተሯ ገልፀዋል፡፡
በተጨማሪም በፕሮጀክቱ ስራ ላይ የሚሳተፈው ቦርድ የመሰረዝ ስልጣን ሳይኖረው 11.1 ሚሊዮን ብር የሚሆኑ የኮፖን ትኬቶችን ጠፉ በሚል ምክንያት መሰረዛቸዉን እና 9.1 ሚሊዮን ብር ለተለያዩ የስራ ማስኪያጃ ከህዝብ እና ከመንግስት የተሰበሰበ ብር አንቀበልም ማለታቸውንም የፌዴራል ዋና ኦዲተር ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ ጠቁመዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት የቀረበውን የኦዲት ግንኝት ሪፖርት የወሎ ተሪሸሪ ኬር ሕክምናና የማስተማሪያ ሆስፒታል እንደማያምንበት እና በድጋሚ ኦዲት ሊደረግ እንደሚገባ የፅህፈት ቤቱ ፕሬዝዳንት አቶ ጌትነት ጠይቀዋል፡፡
ለፕሮጀክቱ ማስተግበሪያ ከመንግስት የቀረበላቸውንም 9.1 ሚሊዮን ብር ፕሮጀክቱ በጥራት ኦዲት ካልተደረገ እንደማይቀበሉ ነው የፅሕፈት ቤቱ ፕሬዝዳንቱ የገለጹት፡፡
በተለይም በኩፖንና በቶንቦላ የተገኘው ገቢ ለማን እንደተሰጠ ስለሚታወቅ ጊዜ ሳይሰጠው ምላሽ እንዲሰጥበትና ወደ ባንክ ገቢ እንዲደረግ የፌዴራል ዋና ኦዲተር ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ አሳስበዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ