ኅዳር 30 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ከሰሞኑ ተቀማጭነቱን በጄኔቫ ያደረገው የሀገር ውስጥ መፈናቀል መከታተያ ማዕከል ባወጣው ሪፖርት በአፍሪካ የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር በሶስት እጥፍ አድጎ 35 ሚሊዮን ደርሷል ብሏል፡፡
በአፍሪካ ከሚገኙ አጠቃላይ 35 ሚሊዮን ተፈናቃዮች 26 ሚሊየን የሚሆኑት በአምስት ሀገራት ማለትም በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ በኢትዮጵያ፣ በናይጄሪያ፤ በሶማሊያ እና በሱዳን እንደሚገኙም ነው ያስታወቀው፡፡
በሃገሪቱ ያሉ የተለያዩ ግጭቶች መቋጫ እስካላገኙ ድረስ የተፈናቃዮች ቁጥር መጨመሩ አይቀርም ያሉት የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ማዕከል ዋና ዳይሬክተር አቶ ያሬድ ሃይለማርያም ናቸዉ፡፡ ባለፉት ጊዜያት በትግራይ ክልል የነበረዉን ጦርነት ተከትሎ አሁንም ድረስ በአማራ ክልል መቀጠሉ በተመሳሳይ ኦሮሚያ እና ሌሎች የሀገሪቱ አከባቢዎችም የተለያዩ ግጭቶች በመኖራቸዉ የተፈናቃዮች ቁጥር ለመጨመሩ ዋነኛ ምክንያት ነዉ ብለዋል፡፡
አሁንም ድረስ ተፈናቃይ የሆኑ ዜጎች በሰፈሩባቸው የመጠለያ ካምፖች ሳይቀር የእለት ደራሽ ምግብ እንዲሁም በመጠለያ ካምፖች እየደረሰባቸው ባለው ጥቃት አማካኝነት የሰብዓዊ መብት ጥሰት መፈጸሚያ ቦታዎች እየሆኑ ስለመምጣታቸውም አንስተዋል፡፡
ሆኖም አሁን ላይ በሀገሪቷ ያለው የጦርነት ድባብ ላይ ስራዎች መሰራት እንዳለባቸው አመላክተው፤እንደ ማሳያ ብለው ካሰቀመጧቸው ነጥቦች ውስጥ ለዜጎች ደህንነት ጥበቃ የሚሰጥ መዋቅር መዘርጋት እንደሚያስፈልግ አስግንዝበዋል፡፡
የምጣኔ ሀብት ባለሙያዉ አቶ እዮብ አዳሙ በሪፖርቱ መቀመጥ የቻሉ ሀገራት በቆዳ ስፋት እና ያላቸው የህዝብ ብዛት በከፍተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ገልጸው፤ይህም አንዱ በዝርዝር ዉስጥ እንዲቀመጡ የሚደርጋቸዉ ቢሆንም ፤በእነዚሁ ሀገራት ውስጥ እየታየ ባለው ጦርነት እና የተፈጥሮ አደጋ ምክንያት የሚፈናቀሉ ሰዎች ከእለት ወደ እለት መጨመሩ የሚታይ ነዉ ብለዋል፡፡ይህ ከፍተኛ የተፈናቃይ ቁጥር ደግሞ ሃገሪቱ አምራች ሃይሏን እንድታጣ እያደረጋት መሆኑን ገልጸዋል፡፡
አሁንም ድረስ ዜጎች በተፈጥሮ እና ሰዉ ሰራሽ አደጋ ምክንያት እየተፈናቀሉ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይህ ደግሞ የፖለቲካ፤ የማህበራዊ እና የኢኮኖሚ ተሳትፎ ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ ከፍተኛ በመሆኑ ይህን መፍታት የሚያስችል ስራ መስራት ይገባል ተብሏል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ