ኅዳር 30 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግልገል በለስና አካባቢው ይስተዋል የነበረውን ኃይል መቆራረጥ ችግር የሚቀርፍ አዲስ የ33 ሺህ ቫኪዩም ብሬከር በግልገል በለስ ሃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ላይ መገጠሙ ተገለጸ፡፡
በፊት አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው ብሬከር ጋዝ የሌለው በመሆኑ እና በቀላሉ መስመሩ እየከፈተ በማስቸገሩ በክልሉ ባሉ ወረዳዎች ላይ ከፍተኛ የኃይል መቆራረጥ እንዲፈጠር ምክንያት ሆኖ ቆይቷል ተብሏል፡፡
በሃይል ማከፋፈያ ጣቢያ የተገጠመው ብሬከር ለድባጢ እና ለወምበራ ወረዳዎች አስተማማኝ ኃይል ለማቅረብ ያስቻለ ሲሆን ከግልገል በለስ -ድባጢ- ቡሌን እና ወምበራ ወረዳዎች ይስተዋል የነበረውን የኃይል መቆራረጥ ችግር በማስቀረት ለሁለት አመት በወረዳው ነዋሪዎች ሲነሳ የነበረውን ቅሬታ ለመፍታት አግዟል ሲል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል፡፡
ብሬከሩን የመቀየር ስራ በ7 ቀናት የተጠናቀቀ ሲሆን ለብሬከሩ ግዢ ከ130 ሺህ ብር በላይ ወጪ መደረጉ ተጠቅሷል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ