ኅዳር 30 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ኢትዮጵያ በሃገር ደረጃ ያላት የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት 69.5 ከመቶ መሆኑ የተገለፀው መናኸሪያ ሬዲዮ የሃገራችንን የንፁህ ውሃ አቅርቦትን በተመለከተ እየተደረገ ስላለው እንቅስቃሴ በጠየቀበት ወቅት ነው ።
በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የሚኒስተሩ አማካሪ የሆኑት አቶ ሞቱማ መቃሳ በሰጡት ምላሽ ፤ አሁን ላይ በክልልም ሆነ በከተማ የንፁህ ውሃ አቅርቦትን ለማዳረስ በፌዴራል መንግስት ፣ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴርና ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር እየተሰራ መሆኑን ገልፀው፤79.12 በመቶ በከተማ ፣ 66.62 ደግሞ በገጠሩ የሃገሪቱ ክፍል አቅርቦቱ መዳረሱን በመጥቀስ ቁጥሩ አሁን ካለው የህዝቡ መጠን ጋር ተመጣጣኝ ባለመሆኑ ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል ።
አክለውም ጦርነት ባለባቸውና አገልግሎት በተቋረጠባቸው አከባቢዎች መልሶ የማቋቋም ፕሮጀክቶችን ከዮኒሴፍ ጋር በጋራ በመሆን የመስራት ሂደቶች መኖራቸውን በመጥቀስ ከፍተኛ የፋይናንስ አቅምን ስለሚጠይቁ ቢዘገዮም እጥረት ያለባቸውን አከባቢዎችን በመለየት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል ።
የፋይናንስ እጥረትና በፍጥነት እየጨመረ የሚገኘው የህዝቡ ቁጥር አሁን ላይ እየተባባሰ ላለው የውሃ አቅርቦት ማነስ እንደተግዳሮት የሚነሳ መሆኑንም ነው ያመላከቱት ።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ