ኅዳር 30 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የጋና ምክትል ፕሬዝዳንት ማሃሙዱ ባውሚያ ቅዳሜ በተካሄደው ምርጫ መሸነፋቸውን አምነው ተቀብለው፤ አሸናፊውን የቀድሞ ፕሬዝዳንት የነበሩትን የተቃዋሚውን ፓርቲ እጩ ጆን ማሃማን በማሸነፋቸው እንኳን ደስ አሎት ብለዋል። “ህዝቡ ለለውጥ መርጧል“ ሲሉም ተደምጠዋል።
ምርጫው የተካሄደው ሀገሪቱ አስከፊ የኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ ባለችበት፤ መሠረታዊ የፍጆታ እቃዎች ዋጋ እጅግ በተወደደበት፤ ወጣቶች ስራ ለማግኘት በተቸገሩበት እንዲሁም ሀገሪቱም እዳዋን መክፈል የማትችልበት ቀውስ ውስጥ በገባችበት ወቅት ነው ብሏል የቢቢሲ ዘገባ።
የምርጫ ኮሚሽኑ ውጤቱን ለመግለጽ የዘገየ ሲሆን፤ ምክንያቱ ደግሞ የሁለቱ ፓርቲ ደጋፊዎች ሂደቱን እያስተጓጎሉ በመሆኑ ፖሊስ በጊዜያዊነት የምርጫ ጣቢያዎች በጥበቃ ስር እንዲቆዩ በማዘዙ ነው ተብሏል፡፡
የአሸናፊው ፓርቲ ደጋፊዎች አደባባይ ወጥተው ደስታቸውን እየገለጹ ናቸው፡፡
ደጋፊዎቹ በአዲሱ ስርዓት ወጣቱ የስራ እድል እንደሚፈጠርለት፤ መሰረታዊ የፍጆታ ሸቀጦችም ዋጋቸው እንደሚቀንስ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል ሲል ዘገባው አስነብቧል፡፡
ተፎካካሪው የመሃማ ፓርቲ 56 በመቶ ድምጽ ሲያገኝ፤ የገዢው ፓርቲ ደግሞ የ41 በመቶ ድምጽ አግኝቷል።
የገዢው ፓርቲ እጩ በአገሪቱ ሊፈጠር የሚችለውን ውጥረት ለማስቀረት እና ሰላምን ለማስጠበቅ ውጤቱ በይፋ ከመገለጹ በፊት ሽንፈቴን አምኜ ተቀብያለሁ ብለዋል።
በዋና ከተማዋ አክራ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲም የጋና ምርጫ በተሳካ ሁኔታ በመጠናቀቁ እንኳን ደስ አላችሁ የሚል መልዕክት አጋርቷል።
አሸናፊው የ65 አመቱ ጆን ማሃማ ከዚህ ቀደም እ.ኤ.አ ከ2012 እስከ 2017 አገሪቱን በፕሬዚደንትነት መምራታቸው የሚታወስ ነው፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ