ኅዳር 30 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ከአሜሪካው ”NBC” ቴሌቪዥን ጋር ታናንት ቃለ መጠይቅ የነበራቸው ተመራጩ ፕሬዝዳንት በምርጫ ቅስቀሳቸው ቃል በገቡት መሰረት በአራት አመታት የስልጣን ዘመናቸው ወቅት ነው ስደተኞቹን እንደሚባርሩ የገለጹት፡፡
ትራምፕ እርምጃው ስልጣን ከሚረከቡበት የመጀመሪያው ቀን ጀምሮ እንደሚተገበርም አስታውቀዋል፡፡ በአሜሪካ ሕገ-መንግስት 14ኛው ማሻሻያ ላይ የሰፈረውን አንድ በሀገሪቱ ከየትኛውም ስደተኛ የተወለደ ሕጻን በቀጥታ የሀገሪቱን ዜግነት እንዲያገኝ የሚፈቅደውን ሕግም ከህገወጥ ስደተኞች የተወለዱ ሕጻናት ተጠቃሚ እንዳይሆኑ በሚከለክል እንደሚተኩት ዶናልድ ትራምፕ አስታውቀዋል፡፡
ይሁንና ከተቀናቃኛቸው ዴሞክራት ፓርቲ ጋር በጋራ እንደሚሰሩበት የገለጹት የተሟላ መኖሪያ ፈቃድ የሌላቸውና በልጅነታቸው በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ ሀገሪቱ የገቡ ስደተኞች በሀገሪቱ እንዲኖሩ የሚፈቅዱላቸው መሆኑን ነው፡፡
በቃለ መጠየቁ ስለ ሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት ኔቶ በምርጫ ወቅት የተናገሩትን እንደሚተገብሩትም አስታውቀዋል፡፡ ትራምፕ አባል ሀገራቱ ራሳቸውን በሚገባ ካላደራጁና መዋጯቸውን ካልከፈሉ ድርጅቱን እንደሚለቁ መናገራቸው ይታወሳል፡፡ በስደተኞች ላይ ያላቸው አቋም ግን ገፍተው የሚሔዱበት እንደሚሆን ነው የተዘገበው፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ