ኅዳር 28 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ፈረንሳዊው የቀድሞው አሰልጣኝ አርሰን ቬንገር በአሁን ሰአት በአለም አቀፉ የእግርኳስ አወዳዳሪው አካል ፊፋ chief of football development ላይ እየሰሩ እንደሚገኙ ይታወቃል። የላቀ ሀሳብ እና እግር ኳሱን ወደ ተሻለ ምዕራፍ ለማሸጋገር የራሱን ሀላፊነት ለመወጣት በማሰብ በዛው የስራ ዘርፍ ላይ እያገለገለ ይገኛል።
International football association board ወይም የዳኝነት ማህበሩ IFAb ላይ አዲስ ህግ ሊጨመር እንደሚችል እየተገለፀ ይገኛል። ሰአት መግደልን ለማስቀረት የታሰበ አንድ ህግ በእግርኳስ ሊተገበር እንደሚችል እና ሀሳቡንም ቬንገእ እንዳመነጩት ለማወቅ ተችሏል።
አንድ ግብ ጠባቂ ሰአት ለመግደል ኳስ ሲያዘገይ ቢጫ ካርድ እንደሚሰጠው ይታወቃል። ታዲያ ይህ በእንዲህ እንዳለ ኳሱን ይዘው ለ8 ሰከንድ ከቆዩ ለተጋጣሚ ቡድን የማዕዘን ምት እንዲሰጥ የሚያስገድድ ህግ ለመተግበር አስበዋል።
እንደ አርሰናል ላሉ በተለይ ከቆመ ኳስ ልዩነቶችን ለመፍጠር የሚሞክሩ ቡድኖች ህግ መልካም ዜና እንደሚሆን ይገመታል። ይህ ህግ ከወዲሁ በፕሪሚየር ሊጉ ከ21 አመት በታች ውድድሮች እንዲሁም በማልታ ሊግ ተሞክረዋል፤ በቀጣይ የጣልያን ከ20 አመት በታች የሴሪያ ጨዋታዎች ላይ ተግባራዊ ይደረጋል፤ ውጤታማነቱ ከታየ በኋላ ግን በሁሉም የእግርኳስ መድረክ ላይ ተግባራዊ ሊደረግ እንደሚችል ለማወቅ ተችሏል።
ከዚህ በፊት ከOffside ጋር በተያያዘ ወይም ከጨዋታ ውጪ ተብሎ የሚሿሩ ኳሶች ላይ አንድ ተጫዋች ሙሉ ለሙሉ ከመስመር ውጪ ነው የምንለው ሙሉ ሰውነቱ ከተከላካዩ ፊት ከሆነ እንጂ ጣቱ ፣ እጁ እንዲሁም ጣቱ ገብቷል በሚል ሳይለካ ሙሉ ሰውነቱ ከገባ ግን ታይቶ ፍርድ ይሰጥበት የሚለውን ሀሳባቸውን ለምክር ቤቱ ማቅረባቸው አይዘነጋም። ወጥነት የሌለው የVAR ውሴኔዎችን ያሻሽላል ተብሎ ቢታመንበትም ምን ያክል ተቀባይነት ያገኛል የሚለው በቀጣይ የሚወሰን ይሆናል መባሉ አይዘነጋም። ይህም በእግርኳሱ ትልቅ ለውጦችን ያመጣል ተብሎ እንደሚገመትም ተመላክቷል፡፡
ለግብ ጠባቂዎች ሰቆቃ ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀው አዲሱ ህግ በተለይ ሰአት የማጥፋት እንቅስቃሴን የሚያዘወትሩ ግብ ጠባቂዎች ማዕዘን ምት የሚያሰጥባቸው ሲሆን ይህም በእግር ኳስ ሌላ ትልቅ ለውጥን እንደሚያስከትል እየተነገረ ይገኛል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ