ኅዳር 28 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) አዲሱ የ39 አመቱ ፖርቹጋላዊ አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ዩናይትድን በአሰልጣኝነት ከተረከበ በኋላ በፕሪሚየር ሊጉ 1 ጨዋታ ሲያሸንፍ 1ዱን አቻ ወጥቶ ከአርሰናል ጋር ያደረጉትን ጨዋታ ሽንፈት አስተናግዷል።
ታዲያ አሰልጣኙ ባለፉት 4 ጨዋታዎች ብቻ 21 የተለያዩ ተጫዋቾችን ተጠቅሟል። ባለፉት 3 ጨዋታዎች ደግሞ በየ ጨዋታው 6 የተለያዩ የተጫዋቾች ለውጥን እናደረገ ነው ወደ ሜዳ ሲገባ የተመለከትነው። ዛሬ ከኖቲንጋም ፎረስት ጋር የሚያደርጉት ተጠባቂ የኦልድትራፎርድ ፍጥጫ በፊት ሀሳቡን የሰጠው አሰልጣኙ ተጫዋቾችን Rotate በማድረግ መሞከር አቁሞ ቋሚ 11 ተመራጭ ተጫዋቾቹን ለመምርጥ ተቃርቤአለሁ ሲሉ ሀሳብ ሰጥተዋል።
ሁሌም እየተማርኩ ነው ሁሌም አዲስ ነገር ነው ማየው ጨዋታ ስናሸንፍ እንኳን የምንሳሳታደው ነገሮች አሉ ፤ ከአርሰናል ጋር የቆመ ኳስ ዋጋ አስከፍሎናል ስለዚል ለመሻሻል ሰፊ መድረኮች ይኖሩናል የዛሬውንም ጨዋታ ሙሉ 3 ነጥብ ለማሳካት ወደ ሜዳ እንገባለን ሲል ሀሳቡን ሰጥቷል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ