ኅዳር 27 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በመዲናዋ 6 ሚሊየን 44ሺህ 402 ብር የሚያወጣ ግምት ያላቸው የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፉ ምግብና መጠጦች ናቸው የተወገዱት።
የአዲስ አበባ ምግብና መድሀኒት ቁጥጥር ባለስልጣን አምራች እና ነጋዴዎች የሚያመርቷቸው እና የሚያከፋፍሏቸው ምግብ እና መድሐኒቶች የህብረተሰቡን ጤና በጠበቀ መልኩ መዘጋጀታቸውን ማረጋገጥ እንዳለባቸው ገልጿል፡፡
ባለስልጣኑም ችግሮች እንዳያጋጥሙ የተቀናጀ የቁጥጥር፤ ክትትል እና ምርመራ ስራ እንደሚሰራ ገልጿል።
ተቋሙ በመጀመሪያው ሩብ አመት አፈጻጸም በመላው አዲስ አበባ በ12ሺ 878 የምግብ አምራች እና አከፋፋይ መሸጫ መደብሮች እንዲሁም ጤና ነክ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ ምርመራ ማድረጉን ገልጿል፡፡
ቁጥጥር እና ምርመራው ከጥቃቅን ምግብ ቤቶች እስከ ባለኮከብ ሆቴሎች ድረስ የተደረገ መሆኑንም ነው በባለስልጣኑ የምግብና ጤና ነክ ተቋማት ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ እስጢፋኖስ ጌታቸው የገለጹት፡፡
በዚህም ጥራታቸውን ያልጠበቁ ምርቶችን ሲያመርቱ እና ሲያከፋፍሉ በተገኙ 272 ተቋማት ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ እንደተወሰደባቸው፤ በ2 ተቋማት ደግሞ የንግድ ፍቃዳቸው እንደተሰረዘባቸው ዳይሬክተር አብራርተዋል።
ዳይሬክተሩ ማንኛውም ምግብ እና መጠጥ አምራች፤ አከፋፋይ እና ሻጭ የህብረተሰቡን ጤና በማይነካ መልኩ አገልግሎት እንዲሰጡ አሳስበዋል፡፡
ህብረተሰቡ የሚመለከተውን ማንኛውም ተያያዥ ችግር ለተቋሙ በአጭር የስልክ መስመር 88-64 ላይ መልክት በመላክም ሆነ ቀጥታ በመደወል ቅሬታውን እንዲያቀርብ ጠይቀዋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ