ኅዳር 27 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ባንኩ በቅርቡ ባወጣው መረጃ፣ የአገሪቱ የፋይናንስ ተቋማት የ2 ነጥብ 7 በመቶ ጥቅል አገራዊ እድገት አስመዝግበዋል ብሏል፡፡
የአፍጋኒስታን ኢኮኖሚ ከሁለት አመት ከባድ ቀውስ በኋላ መጠነኛ የእድገት ምልክቶች እያሳየ ነው ሲል የአለም ባንክ ባወጣው መረጃ ገልጿል።
የአገሪቱ የፋይናንስ ተቋማት በአገር ውስጥ ፍጆታ ምክንያት የ2 ነጥብ 7 በመቶው መጠነኛ የሀገር ውስጥ ጥቅል የምርት ዕድገት እንዳሳየም ነው የተገለጸው።
የምግብ ዋጋ መቀነስ በቤተሰብ ደረጃ ያለው የዜጎች ደህንነት ቀስ በቀስ ለማሻሻል ረድቷል ተብሏል። ታሊባን እ.ኤ.አ በነሀሴ ወር 2021 ስልጣን ከመያዙ በፊት የአፍጋኒስታን ኢኮኖሚ በውጪ እርዳታ ላይ የተመሰረተ እንደነበር ዘገባው አስታውሷል።
በሦስት ዓመታት ውስጥ የታሊባን መንግስት የአገሪቱን ኢኮኖሚው ወደ ኋላ አስቀርቷልም ተብሏል፣ በቢሊዮን ዶላር የሚቆጠሩ በጀት የሚሸፍኑ የዓለም አቀፍ እርዳታዎች መታገዳቸው አገሪቱን ጎድቷት ቆይቷል ተብሏል፡፡
እ.ኤ.አ ከ2023-24 አፍጋኒስታን ወደ ውጭ የምትልካቸው ምርቶች መጠነኛ ቢሆኑም ከውጭ የሚገቡት ግን መጠናቸው ጨምሯል ነው የተባለው።
የወጪ እና ገቢ ንግድ ጉድለት አገሪቱን እንደ ነዳጅ፣ ምግብ እና ማሽን ባሉ ከውጭ በሚገቡ ምርቶች ላይ ጥገኛ በማድረግ፣ የአገሪቱን ኢኮኖሚ መረጋጋት አደጋ ላይ ሊጥል ይችላልም ነው የተባለው።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ