ኅዳር 27 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ጊዜያት ከ100 በላይ ሰራተኞች ኮሚሽኑን ለቀው መውጣታቸውን የፌዴራል የሥነ ምግባር እና ጸረ-ሙስን ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
ዝቅተኛ ክፍያ እና የስራ ጫና በርካታ ሰራተኞች ኮሚሽኑን ለቅቀው እንዲወጡ እየገፋፋቸው መሆኑን የፌዴራል የስነ ምግባር እና ጸረ-ሙስና ኮሚሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ሻሜቦ ለመናኸሪያ ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡
በ2015 በኮሚሽኑ ከነበሩ ሰራተኞች ከ100 በላይ የሚሆኑት ስራቸውን ለቅቀው መውጣታቸውን የሚናገሩት የኮሚሽኑ ጽህፈት ቤት ኃላፊው፣ ሰራተኞች ስራቸውን የሚለቁበት ዋናው ምክንያት በኮሚሽኑ ካለው የስራ ጫና ጋር ተመጣጣኝ ክፍያ ባለማግኘታቸው ነው ብለዋል፡፡
በርካታ ሰራተኞች ከኮሚሽኑ ስራ እየለቀቁ ቢሆንም፤ ባለፉት 2 ዓመታት የመንግስት መስሪያ ቤቶች አዲስ ቅጥር እንዳይፈጽሙ በተላለፈው ውሳኔ ምክንያት በሚለቁ ሰራተኞች ቦታ መተካት እንዳልተቻለ አቶ ተስፋዬ ተናግረዋል፡፡
በዚህም ተቋሙ ለሚያከናውናቸው ተግባራት የሰው ኃይል እጥረት ፈተና እንደሆነበት ነው የተናገሩት፡፡
ይህን ያህል ሰራተኞች ኮሚሽኑን ለቅቀው ሲወጡ፣ ለመንግስት አላሳወቃችሁም ወይ? ጠይቃችሁ ከሆነስ ምልሹ ምን ነበር ሲል መናኸሪያ ሬዲዮ ላቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ የሰጡት፣ የኮሚሽኑ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋዬ፣ የሰራተኞችን ችግር እና ቅሬታ በተደጋጋሚ ለመንግስት ቢያቀርቡም ምላሹ እንደዘገየ ነው የገለጹት፡፡
መንግስት የኮሚሽኑ ሰራተኞች ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ይሰጣል የሚል እምነት እንዳላቸው ገልጸው፣ የህበረተሰቡን ችግር ለመፍታት በእውቀት የተገነቡ ከስራ ባህሪያቸው ጋር ተመጣጣኝ የሆነ ክፍያ የሚያገኙ ሰራተኞች እንደሚያስፈልጉ አመላክተዋል፡፡
የሰራተኛ ፍልሰት እና ሌሎች ተያያዥ ችግሮች ለኮሚሽኑ ተግዳሮት ቢሆኑም ከክልልና ከተማ መስተዳደር የስነ ምግባር እና ጸረ-ሙስና ኮሚሽን ቢሮዎች ጋር በመነጋገር እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ