ኅዳር 26 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በኢትዮ ሶማሊያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ኃላፊነት የተሞላበት እርምጃ እንደሚወሰድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል።
የሶማሊያ መከላከያ ሚንስትር አብዱልቃድር ሞሐመድ ኑር በሀገራቸው መገናኛ ብዙሃን ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ጋር የተፈራረመችውን የባሕር በር የመግባቢያ ስምምነት ካልሰረዘችና ወታደሮቿን ካላስወጣች ከመጪው ታኅሳስ ወር ጀምሮ እንደ ወራሪ ሃይል እንደሚቆጥሯት መናገራቸውን ገልጸዋል።
ይህንን ተከትሎ የኢትዮጵያ አቋም ምን ሊሆን ይችላል በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባዩ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው ኢትዮጵያ ኃላፊነት የተሞላበት እርምጃን እንደምትወስድ ነው የተናገሩት።
አምባሳደር ነቢያት ከሶማሊያ በኩል በየጊዜው ኃላፊነት የጎደላቸው ተንኳሽ ንግግሮች ቢሰሙም ኢትዮጵያ ጉዳዩን የማለዘብ እና በእርጋታ የመመልከት ስራ ስትሰራ ቆይታለች ብለዋል።
ወደ ፊትም ጉዳዩን በእርጋታ በመመልከት እንደሚሰራ የተናገሩት ቃል አቀባዩ፤ ከሌሎች አጋር አካላት ጋር በመሆን የአልሸባብን ስጋት ግምት ውስጥ ያስገባ እንቅስቃሴ እንደሚሰራ እና ይህም መሆኑ ለቀጠናው ብቻ ሳይሆን ከቀጠናውም የተሻገረ ሰላም እንደሚያሰፍን ገልጸዋል።
አሁን ላይ ባለው ፖለቲካዊ ዲፕሎማሲ ምክንያት ሰሞኑን ኮሎንቢያ እና ስሎቬንያ በአዲስ አበባ ኤንባሲያቸውን እንደሚከፍቱ የገለጹት ቃል አቀባዩ፤ በዚህም በአዲስ አበባ የሚገኙ የኤንባሲዎች ቁጥር ወደ 137 ከፍ ማለቱን አስታውቀዋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ