ኅዳር 26 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በሊባኖስ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን ወደ አገር የመመለሱ ስራ መጀመሩን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው ዛሬ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
በሊባኖስ ለደህንነታቸው አስጊ በሆነ ሁኔታ የሚኖሩ ዜጎችን ለማስመለስ ተግባራዊ ስራ ተጀምሯል ሲሉም ነው አምባሳደር ነቢያት የተናገሩት።
ከህዳር 22 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ 2ሺ የሚሆኑ ዜጎችን ወደ አገር ለመመለስ የበረራ እንቅስቃሴዎች መጀመራቸውን የገለጹት ቃል አቀባዩ፤ ከዛሬ ህዳር 26 ቀን ጀምሮ ተግባራዊ የሆነ ዜጎችን የማስመለሱ ስራ እንደሚጀምርም አስታውቀዋል።
በቤሩት በህገ ወጥ መልኩ ሲኖሩ የነበሩ ዜጎች ከአገሪቱ ሲወጡ ለኖሩበት ጊዜ የሀገሪቱ መንግስት የሚያስከፍለውን ክፍያ አቅምን ያገናዘበ እንዲሆን በቤሩት የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዲፕሎማሲያዊ ንግግር እያደረገ ነው ብለዋል።
በተመሳሳይ በሕገ-ወጥ አዘዋዋሪዎች ምክንያት ወደ ማይናማር የተጓዙና በዚያ የታገቱ ኢትዮጵያውያንንም ለማስለቀቅና ለማስመለስ ከሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለስልጣናት ጋር ጃፓን በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አማካኝነት ውይይት መደረጉንና ንግግሩ አዎንታዊ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባዩ ገልጸዋል።
የዜጎችን ደህንነት ማስጠበቅ ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲን ለሚከተል መንግስት ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር መሆኑን አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው ዛሬ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ