ኅዳር 26 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ የህንፃ አዋጅን ለማፅደቀ የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 1356/2017 በ6ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ስብሰባ በሙሉ ድምፅ ጸድቋል፡፡
ላለፉት አመታት የሪል እስቴት ገንቢዎች ከመንግስት መሬት እየወሰዱ ግንባታቸው ሳይጠናቀቅ ለገዢዎች ሲያቀርቡ እንደነበር የሚናገሩት የምክር ቤቱ አባል ዶክተር እሸቱ ተመስገን ገዢዎችን ላልተገባ ኪሳራ እየዳረገ በመሆኑ ከ80 በመቶ በላይ ግንባታቸው ካልተጠናቀቀ ለሽያጭ እንደማይቀርቡ የሚደነግግ ረቂቅ አዋጅ መጽደቁ ተገቢ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ረቂቅ አዋጁ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ የሪል እስቴት ገንቢዎች በግንባታ ፍቃድ ሳይሆን የሪል እስቴት ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ካልያዙ ግንባታ ማከናወን እንደማይችሉም ተገልጿል፡፡
በአዲሱ ረቂቅ አዋጅ የሪል እስቴት ዘርፍ አልሚዎች ከ250 እስከ 2ሺህ 500 ቤቶችን በሪል እስቴት ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት መገንባት እንደሚችሉም ተጠቁሟል፡፡ የተሻሻለው ረቂቅ አዋጅ የደንበኞችን መብት እንደሚያስጠብቅ እና የሽያጭ ዋጋቸውም ባለው ነባራዊ የዋጋ ሁኔታ እንደሚወሰን ነው የተገለጸው፡፡
በኢትዮጵያ የሪልስቴት ዘርፉ ወደ ኋላ የቀረ መሆኑንና በሃገር ደረጃ አሰራሩ የተዳከመ በመሆኑ የአዋጁ መሻሻል አስፈላጊ እንደሆነ በምክር ቤቱ ተመላክቷል፡፡
በአዲሱ አዋጅ የተገለጹ የህግ ማዕቀፎችና ቅጣቶች በመሬት ይዞታ የሚስተዋሉ የእጅ መንሻ የሙስና ድርጊቶችን መቆጣጠር የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ