ኅዳር 26 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በደቡብ ምዕራብ ዲሞክራቲክ ኮንጎ ጉንፋን መሰል ምልክቶችን እየፈጠረ ባለው ባልታወቀ በሽታ ቢያንስ ከ79 በላይ ሰዎች መሞታቸውን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ከሟቾች መካከል አብዛኞቹ ከ15 እስከ 18 ዓመት መካከል ያሉ ታዳጊዎች መሆናቸውን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ገልጿል።
ከ300 በላይ ሰዎች እንደ ትኩሳት፣ ራስ ምታት፣ የአፍንጫ ፍሳሽ እና ሳል፣ የመተንፈስ ችግር እንዲሁም የደም ማነስ ምልክቶች ታይቶባቸዋል ነው የተባለው።
የህክምና ባለሙያ ቡድኖች በአገሪቱ ወደ ክዋንጎ ግዛት በተለይም በሽታው በብዛት ወደተስፋፋበት የፓንዚ ጤና ዞን ስርጭቱን ለመቆጣጠር እና የበሽታውን ምንነት ለመመርመር ተልከዋል።
የሲቪል ማህበረሰብ መሪ የሆኑት ሴፎሪን ማንዛንዛ ለሮይተርስ እንደተናገሩት በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ ሁኔታው አሳሳቢ መሆኑን ገልጸዋል።
የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) በአፍሪካ የተከሰተውን ጉንፋን መሰል ወረርሽን ምንነቱን እያጣራ እንደሆነ ዘገባው ገልጿል፡፡
የጤና ባለሙዎች ሰዎች ከቫይረሱ ራሳቸውን ለመከላከል እጃቸውን በሳሙና እንዲታጠቡ፣በጅምላ ከመሰብሰብ እንዲቆጠቡ፣ የሟቾችን አስክሬን ከመንካት እንዲቆጠቡ አሳስበዋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ