ኅዳር 26 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ተጨማሪ የመንግስት ድርጅቶችን በስሩ እንዳከተተ ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል፡፡
ድርጅቱ በሚኒስትሮች ምክር ቤት በተሰጠው ስልጣን መሰረት የልማት ድርጅቶችና ሃብቶችን ለበለጠ ተግባር ለማዋል እንዲቻል በስሩ እያካተተ መሆኑን የተቋሙ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሀብታሙ ሃይለሚካኤል ተናግረዋል፡፡
ድርጅቶቹን ወደ አንድ በማምጣት በተቋማቱ ውስጥ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመፍታት የተሻለ ለውጥ ለማምጣት ስራዎች መጀመራቸውን አመላክተዋል፡፡ተቋማቱ ምን ያስፈልጋቸዋል የሚለዉን እና ችግሮችን በመለየት መፍትሄ አምጪ ስራዎች እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሀብታሙ ሀ/ሚካኤል አክለውም፤ተቋሙ በስሩ ያካተታቸው የመንግስት ድርጅቶች የፋይናንስ ችግሮቻቸው ላይ ጥናት እየተደረገ መሆኑን በመግለፅ ድርጅቶቹ ያለባቸው ጠቅላላ የሂሳብ ስራዎች እየተጠናቀቀ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ኢትዮ ፖስታ፤ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ፤የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብአቶች ልማት ድርጅት ፤የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን፤የኢንድስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን፤የኢትዮጵያ ልማት ባንክ፤የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ኮርፖሬሽን እና ለኢትዮ ፋርም ግሩፕ በኢንቨስትምንት ሆሊዲንግስ መካተታቸው ተገልጿል፡፡
በቀጣይ ሌሎች የመንግስት የልማት ድርጅቶችን የማካተት ስራ እንደሚቀጥልም ጨምረው ገልፀዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ