ኅዳር 25 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በ7 ክፍሎችና በ64 ዝርዝር ጉዳዮች ላይ ያዘጋጃቸውን አጀንዳ በዛሬው እለት ለኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስረክቧል፡፡
የሃገረ መንግስት ግንባታና የሃገርን አንድነት በሚመለከቱ ጉዳዮች፤ ህገ-መንግስዊ ፤ ኢኮኖሚያዊ ፤ማህበራዊና ባህላዊ ጉዳዮች ፤ የተቋማት ግንባታ፤ የማንነት አስተባበር ወሰንና የክልልነት ጉዳዮች፤ የውጭ ግንኙነትና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የሚል 7 ክፍሎች የያዘ 64 ዝርዝር ጉዳዮች ለምክክር ኮሚሽኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን አየለ አቅርበዋል፡፡
ምክር ቤቱ ዛሬ ለኮሚሽኑ ያስረክባቸው አጀንዳዎች በምክርቤቱ በሙሉ ድምፅ የፀደቁ መሆናቸውን አንስተው የተደራጁት የፖለቲካ ፓርቲዎች አጀንዳዎች ለአካታችና አሳታፊው ሀገራዊ ውይይት የሚያግዙ እንደሚሆኑም ገልፀዋል፡፡
የጋራ ምክር ቤቱ ያቀረባቸውን አጀንዳዎች የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ተረክበዋል። ዋና ኮሚሽነሩ የምክክር ኮሚሽኑ ከምክር ቤቱ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሞ በጋራ እየሰራ መሆኑን አንስተው በተቋማትና በማህበረሰብ ክፍሎች ተደራጅተው የሚቀርቡ አጀንዳዎችን በአግባቡ እንደሚጠቀምባቸውም ተናግረዋል፡፡
በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ ከ350 በላይ ወረዳዎች ከታህሳስ 5 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ አጀንዳ ማሰባሰብ እንደሚከናወን ዋና ኮሚሽሩ አንስተው የፌዴራል ባለድርሻ አካላትም አጀንዳዎቻቸውን ለኮሚሽኑ ያቀርባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተመላክቷል፡፡
ሌሎች ተቋማትና ማህበራትም የተደራጁ አጀንዳዎቻቸውን እንዲያስረክቡ ዋና ኮሚሽነሩ ጠይቀዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ