ኅዳር 25 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ፍልስጤማውያን ፋታህ እና ሃማስ ከጦርነቱ በኋላ ለጋዛ አስተዳደር እቅድ ቅርብ ናቸው ይላሉ።
የፍልስጤም ባለስልጣናት ትላንት እንዳሉት ፋታህ እና ታጣቂው ቡድን ሃማስ ከጦርነቱ በኋላ ጋዛን የማስተዳደር እቅድ ላይ ከስምምነት ላይ ደርሰዋል።
እቅዱ በእስራኤላውያን ቁጥጥር ስር የሚገኘውን ዌስት ባንክን በከፊል የሚያስተዳድረው ፋታህ እና ከ2007 ጀምሮ ጋዛን የተቆጣጠረው ሃማስ እስከ 15 የሚደርሱ ከፖለቲካ ነፃ የሆኑ ቴክኖክራቶች ያሉት ኮሚቴ የጋዛ ሰርጥን እንዲያስተዳድር በጋራ የመሾም እቅድ እንዳላቸዉ ታይቷል። ባለሥልጣናቱ ዕቅዱ ከእስራኤል ጋር የተኩስ አቁም ስምምነትን ተከትሎ ነው ብለዋል።
በጋዛ ያለውን ጦርነት ለማስቆም በዩናይትድ ስቴትስ፣ ግብፅ እና ኳታር አስተባባሪነት የወራት ድርድር በእስራኤል እና በሃማስ መካከል ሲደረግ ቆይቶ ስምምነት ላይ መድረስ አልተቻለም።
ዩናይትድ ስቴትስ እና ሌሎች ባለስልጣናት በእስራኤል እና በሊባኖስ ላይ በሚገኘው የሂዝቦላ ታጣቂ ቡድን መካከል የተኩስ አቁም ስምምነት በጋዛ ለማስፈጸም ጥረትና ተስፋ ላይ ናቸዉ ተብሏል።
የተኩስ አቁም ስምምነቱ እስራኤል ጦሯን ከሊባኖስ እንድታስወጣ እና ሄዝቦላህ ተዋጊዎቿን ከድንበር እንዲያንቀሳቅስ ይጠይቃል። የሊባኖስ ወታደራዊ እና የተባበሩት መንግስታት የሰላም አስከባሪ ሃይሎች በሁለቱ ወገኖች መካከል ያለውን የጥበቃ ቀጠና ለመከታተል ተዘጋጅተዋል ሲል የዘገበው አልጀዚራ ነው፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ