ኅዳር 25 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ኔቶ የሩስያ እና ቻይናን አጠቃላይ እንቅስቃሴን ማስተጓጎል እና መከላከል የሚያስችል የስለላ ትብብርን እንደሚያሳድግ እና እንደሚተገብር የኔቶ የምዕራብ ወታደራዊ ህብረት ሃላፊ አስታወቁ።
ትላንት ብራሰልስ ውስጥ የኔቶ ግዛቶች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በተሰበሰቡበት ወቅት ማርክ ሩት እቅዱን ገልፀዋል ። ስዊድንን እና ፊንላንድን የሚያገናኘው የመረጃ ገመድ ላይ የደረሰውን ጉዳት በተመለከተ ጥያቄዎች ሲነሱ የቆየ ሲሆን የሁለቱ ሃገራት ሴራ ሳይሆን እንዳልቀረ ተገምቷል፡፡
ባለፉት አመታት ሩሲያ እና ቻይና እኛን ለማስፈራራት በሳይበር ጥቃት፣ በሀሰት መረጃ እና በሃይል ማጭበርበር ሀገሮቻችንን ለማተራመስ ሞክረዋል ብለዋል። የኔቶ አጋሮች ከፍተኛ የስለላ መጋራትን እና ወሳኝ መሠረተ ልማቶችን የተሻለ ጥበቃ ማድረግን ጨምሮ በተለያዩ እርምጃዎች እነዚህን አደጋዎች ለመቋቋም በአንድነት መቆማቸውን ይቀጥላሉ ሲሉም አክለዋል፡፡
የኔቶ የስለላ መጋራት ግፊት የመጣው በስዊድን እና በፊንላንድ ያሉ ባለስልጣናት ሁለቱም ሩሲያ በየካቲት 2022 በዩክሬን ላይ ሙሉ ወረራ ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ የድንበር ተሻጋሪ ገመድ እንዴት እንደተቆረጠ ሲመረምር ከቆየ በኋላ ነዉ ተብሏል፡፡ ሁለቱም ሃገራት ደግሞ በዚሁ ወቅት ህብረቱን መቀላቀላቸዉ ይታወሳል።
በመሬት ላይ የተመሰረተው የፋይበር ኦፕቲክ ትስስር ባሳለፍነዉ ሰኞ በሁለት ቦታዎች ላይ ጉዳት እንደደረሰበት ታዉቋል፡፡ የፈጠረው መቆራረጥ በሺዎች የሚቆጠሩ ደንበኞችን አገልግሎት አቋርጧል ሲሉ ሃላፊዉ ተናግረዋል ሲል የዘገበው አልጀዚራ ነዉ፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ