ኅዳር 25 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ከታኅሳስ 01 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በመዲናዋ ተግባራዊ የሚደረግ የ100 ፐርሰንት ጭማሪ ማድረጉን ይፋ አድርጓል፡፡ የባቡር ትራንስፖርቱ በተገልጋዮች የተለያዩ ቅሬታዎች የሚነሱበት እንደመሆኑ ከታሪፍ ጭማሪዉ ጎን ለጎን የአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሺያ ላይ ምን ተሰርቷል የሚለዉን መናኸሪያ ሬዲዮ ለአገልግሎቱ ጥያቄ አቅርቧል፡፡
የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ብርሃኑ አበባው አገልግሎቱን ለማሻሻል በእቅድ ደረጃ የታሰቡ ነገሮች ቢኖሩም አሁን ላይ የሚተገበር ነገር እንደሌለና ወደፊት ግን አገልግሎቱን ለማሻሻል በሚሰራዉ ስራ የባቡሮችን ቁጥር ከፍ ለማድረግ መታቀዱን አስረድተዋል፡፡
በተጨማሪም አገልግሎት መስጠት ያቆሙ ባቡሮችን ወደስራ ለማስገባት መታቀዱን በመግለፅ ፤ አሁን ላይ ከ 60 ሺሕ በላይ ለሚሆኑ ተሳፋሪዎች አገልግሎት የሚሰጠዉን ተቋም ተገቢዉ የፋይናንስ አደረጃጀት እንዲኖረዉ ለማስቻል በተለይም በመለዋወጫና በኤሌክትሪክ ፍጆታ ላይ የተፈጠረውን ቀውስ ለመቀነስ የታሪፍ ጭማሪዉ እንደተደረገ ተናግረዋል፡፡
ከሰሞኑ በትኬት አጠቃቀም ላይ ቁጥጥር እንደጀመሩና እስከ ምሽት ሳይከፍሉ የሚሳፈሩ ተገልጋዮችን የመቆጣጠር ስራ በተቀናጀ መልኩ እየተከናወነ መሆኑን አስተድተዋል፡፡ አሁን የተደረገዉ ጭማሪ 10 በመቶ የሚሆነዉን የፋይናስ ፍላጎት ማሟላት እንኳን እንደማይችል ጠቅሰዉ በመጪው ሰኔ ወር 2017 ዓ.ም መጨረሻ 21 ባቡሮች በተጨማሪነት የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጡ ይደረጋል ብለዋል፡፡
የምጣኔ ሃብት ባለሙያው አቶ እዮብ አዳሙ የተደረገዉ የታሪፍ ጭማሪ የሚጠበቅ ነዉ ያሉ ሲሆን ምክንያታቸዉንም ሲገልጹ በአለማችን ላይ ባለው የገንዘብ እንቅስቀሴ ምክንያትና የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ የሚደረጉ ማስተካከያዎች የታሪፍ ጭማሪ እንዲደረግ ያስገድዳሉ ብለዋል፡፡ የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር የትራንስፖርት አግልግሎት ደግሞ በራሱ የሚተዳደርና ከመንግስት ዝቅተኛ በጀት የሚቀበል በመሆኑ የሚኖርበትን ወጪ ከማመጣጠን አንፃር ጭማሪውን ተጠባቂ ደርገዋል ሲሉም ገልጸዋል፡፡
የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር በኪሳራ የሚሰራ እና ከፍተኛ ቅሬታ የሚነሳበት ተቋም እንደመሆኑ የታሪፍ ጭማሪዉ ተጠባቂ ቢሆንም የአግልግሎት ማሻሺያዉ አብሮ ሊተገበር እንደሚገባ ተመላክቷል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ