ኅዳር 24 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በመዲናዋም ሆነ እንደ ሀገር የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት እጥረት መኖሩ በተደጋጋሚ የሚነሳ ነው፡፡
የግል ባለሀብቶች ንጹህ መጠጥ ውሃን አሽጎ በመሸጥ ስራ ላይ በስፋት መሰማራታቸውን በውሃና ኢነርጅ ሚንስቴር የሚንስትሩ አማካሪ አቶ ሞቱማ መቃሳ ለመናኸሪያ ሬዲዮ ገልፀዋል፡፡
ይሁን እንጂ ከዚህ ቀደም የነበረው ፖሊሲ የከርሰ ምድር ውሃን አውጥቶ መሸጥን እንደሚከለክል ነው ያስታወቁት፡፡
ፖሊሲው ከ20 ዓመት በፊት የወጣ በመሆኑ አሁን ላይ ወቅቱን ስለማይመጥን ማሻሻያ መደረጉን እና እስኪፀድቅ እየተጠበቀ እንዳለ ገልጸዋል፡፡
የውጪ ሀገራት ድጋፍ ሰጪዎች፤ አበዳሪዎች እንዲሁም መንግስት ለመጠጥ ውሃ አቅርቦት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራበት ቢሆንም የቁፋሮ ስራው በባለሃብቶች አሊያም በግል ድርጅቶች እንዲከናወን እንደሚደረግ አስታውቀዋል፡፡
በዚህ ረገድ የአቅርቦት ውስንነት እንዳለ የገለጹት አቶ ሞቱማ፤ አሁን ላይ መሻሻል ቢኖረውም በበቂ ሁኔታ አቅም ያላቸውን ማግኘት አለመቻሉን እና በሚኒስቴሩም በኩል ይህን ለማሻሻል እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የግል ባላሃብቶች በሌሎችም ትልልቅ በሚባሉ የኮንትራት ስራዎች አቅማቸው እንዲዳብር እንዲሁም በውሃ አቅርቦቱ ዙሪያ ተሳታፊ እንዲሆኑ እየተሰራ መሆኑን ኃላፊው ገልጸዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ