ኅዳር 24 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የ32 አመቱ ግብፃዊው ኮከብ ሞሀመድ ሳላይ የፈረንሳዩን ሀያል ክለብ ለመቀላቀል ይፋዊ በሆነ መልኩ ንግግሮችን መጀመሩ ተገልጿል።
ሞ ሳላህ ከኮንትራት እድሳት ጋር በተያያዘ ከክለቡ ጋር የገባበት አለመግባባት ይፋ መውጣቱ የአደባባይ ሀቅ ከሆነ የሰነባበተ ጉዳይ ሆኗል።
እድሜው 30ዎቹን ቢያልፍም እንደ ወይን እያደረ እየጣፈጠ የሄደ ድካም ፤ መቀዝቀዝ የማይታይበት ልዩነት ፈጣሪው ኮከብ ነው። ታዲያ በአንፊልድ የነበረውን የ8 አመት ቆይታ ሊቋጭ ስለመሆኑ እየተገለፀ ይገኛል።
የሳውዲ ፕሮ ሊግ እንዲሁም የሜጀር ሊግ ሶከር ክለቦች አሰፍስፈው ተጫዋቹን ለማስፈረም ፍላጎት እንዳላቸው ቢያሳዩም ተጫዋቹ ግን ሜዳ ላይ የሚያሳየው ይህ እንቅስቃሴውን ይዞ በዚህ ሰአት ከአውሮፓ መውጣት አይፈልግም ተብሏል።
ታማኙ የሀገሪቱ ሚዲያ ላኪፕ ደግሞ ተጫዋቹ የሚፈልገው አይነት ኮንትራት ክለቡ ሊቀርብለት ባለመቻሉ መንገዱን ጨርቅ ያድርግልህ ተብሎ እንደተነገረው እንደሚቆጥረው እና ከወዲሁ ከፒኤስ ጂ ጋር ንግግሮችን ጀምሯል ሲል ዘግቧል።
ማርከስ ራሽፈርድ ፤ ክቪካ ክቫርሽኬሊያ ፤ ኒኮ ዊሊያምስ ፤ ጄደን ሳንቾ እነዚህን ተጫዋቾች በተለያዩ ጊዜያቶች ላይ ለማስፈረም እየፈለገ ያልቻለው ፓሪስ ሴንት ጄርሜ አሁን ግን ግብፃዊው ኮኮብ ሞ ሳላህን ለማስፈረም ጠንክረው የቀረቡ ይመስላል፡፡ የዝውውር ሂሳብ ሳይከፍሉ በክረምቱ ተጫዋቹን በነፃ የማግኘት እቅድ እና ፍላጎትም ነው ያላቸው።
በግራ መስመር ላይ ከኦሎምፒክ ሊዮን የሸመቱት ብራድሊ ባርኮላ መልካም የሚባል የሜዳ ላይ እንቅስቃሴ የሚያሳየው ተጫዋች ነው። በቀኝ መስመር የአጥቂ ቦታ ላይ ግን ኦስማን ዴምቤሌ ወጥነት ያለው የሜዳ ላይ እንቅስቃሴ ማሳየት ያልቻለው ተጫዋች ነው።
በአጠቃላይ ኪሊያን ምባፔ ክለቡን ከለቀቀ በኋላ የፒኤስጂ አስፈሪ የማጥቃት መስመር ተመናምኖ እየተመለከትነው እንገኛለን። ስለዚህ መልሰው በፊት የነበራቸውን ግርማ ሞገስ ለመላበስ እንዲሁም እዚ ክለቡ ውስጥ በጥብቅ የሚፈለገው የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ ክብር ለማሳካት እንደ ሞ ሳላህ አይነት ልምድን ከጥሩ አቅምና ብቃት እንዲሁም ክህሎት ጋር አዋህደው የሚገኙ ተጫዋቾችን ማግኘት ግድ ይላል ለዛም ነው ፒኤስ ጂዎች ሞ ሳላህን በእጁ ለማስገባት ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ የሚገኙት ተብሏል፡፡
በሚያከናውናቸው ጨዋታዎች ሁሉ በተለይ ከጨዋታው በኋላ ሞ ሳላህ ሀሳብ ሲሰጥ ሁሌም በክለቡ እንደማይቆይ ፤ ኮንትራት እንዳልተሰጠው ነው የሚናገረው። ባሳለፍነው እሁድ ማንቸስተር ሲቲን 2-0 ካሸነፉ በኋላ “በሊቨርፑል ማልያ አንፊልድ ላይ ሲቲን በተቃራኒ የማገኝበት የመጨረሻ መርሀ-ግብር ነው ብዬ ነው የማስበው ስለዚህ ፤ እያንዳንዱን ደቂቃ ደግሞ እያጣጣምኩ እና ደስ እያለኝ ነው ማሳለፍ የምፈልገው” ሲል ሀሳብ መስጠቱ አይዘነጋም።
ሳላህ በሁሉም ጨዋታዎች ባደረገው 20 ጨዋታ 13 ጎል ሲያስቆጥር 11 ኳስ አመቻችቶ ማቀበል ችሏል። ሊቨርፑል ይህንን ተጫዋች የትኛውንም መስዋትነት ከፍሎ ማለትም ተጫዋቹ ያስቀመጣቸውን መስፈርቶች በማሟላት ለማቆየት ያልሄዱበት ጥረት ያስቆጫቸዋል ፤ ወይስ ትክክለኛ ውሳኔ ነው የወሰኑት የሚለው ጊዜ የሚፈታው ጉዳይ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ