ኅዳር 24 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ሁለቱ የሊጉ ተወዳጅነት መንስኤዎች እንዲሁም በሀገራችን ኢትዮጵያም ሆነ በአህጉራችን አፍሪካ በርካታ ደጋፊዎች ያሏቸው ሁለቱ ክለቦች ነገ ከሚያከናውኑት ተጠባቂ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ በፊት በኤፍ ኤ ካፑም እንደሚገናኙ ለማወቅ ተችሏል።
ትላንት በኦልድትራፎርድ በወጣው የእጣ ማውጣት ስነ ስርአት አርሰናል በኤፍ ኤ ካፕ 3ኛ ዙር ማንቸስተር ዩናይትድን እንዲያስተናግዱ እጣ ድልድላቸው ይፋ ሆኗል።
ሁለቱ ቡድኖች በዚህ የውድድር መድረክ ለ16 ጊዜ ተገናኝተዋል ፤ ዘንድሮ 17ኛቸው ይሆናል። አርሰናል 14 ጊዜ ይህንን ክብር በማሳካት የሚመራው ክለብ ሲሆን ዩናይትድ አምና ያሳካውን ክብር ለማስጠበቅ ጉዟቸውን ከሜዳቸው ውጪ አርሰናልን በማግኘት የሚጀምሩ ይሆናል።
ጨዋታዎቹ የፊታችን ጥር ወር ላይ የሚከናወኑ ይሆናል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ