ኅዳር 24 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ባለፉት ጊዜያት በመዲናዋ በቤቲንግ ውርርድ ዘርፍ የተሰማሩ አካላት ህገ-ወጥ ድርጊትን መቆጣጠር ተችሏል ቢባልም፤ አሁንም ድረስ ከመዲናዋ ባለፈ በክልል ከተሞች መስፋፋቱን መናኸሪያ ሬዲዮ ያነጋገራቸው የአማራ ክልል እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር አስታውቀዋል፡፡
የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የሴቶች ህጻናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሁክሚያ መሀመድ ከፍትህ ተቋማት ጋር በመቀናጀት በቤቲንግ ውርርድ ዘርፍ የተሰማሩ ግለሰቦችን የማስቆም እና እርምጃ የመውሰድ ተግባር ቢሰራም አሁንም አመርቂ ውጤት እየተመዘገበ አይደለም ብለዋል፡፡
በከተማዋ በርካታ ቁጥር ያላቸው ፍልሰተኞች እንዳሉ የተናገሩት ኃላፊዋ፤ አብዛኛዎቹ ወደ ጅቡቲ እና አረብ ሀገራት የሚሔዱ ናቸው ብለዋል፡፡
ጉዟቸው ሲሰናከል በከተማዋ በጎዳና ተዳዳሪነት እና በውርርድ ስራ ተሳታፊ እንደሚሆኑ አስታውቀዋል፡፡ በከተማዋ የተደራጀ የመዋያ ስፍራ አለመኖሩን ተከትሎ አሁንም ድረስ በርካታ ነዋሪዎች በቤቲንግ ውርርድ ቤቶች ላይ ውሎ እና አዳራቸውን አድርገዋል ነው ያሉት፡፡
የአማራ ክልል ሴቶች ህጻናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የማህበራዊ ጥበቃ ማስተባበሪያ እና መከታተያ ዳይሬክተር አቶ በላይነህ ጸጋው፤ በክልሉ የውርርድ ቤቶች እየተስፋፉ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
ከህጻናት እስከ ወጣቶች ባሉ የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ አካላት በዚሁ ተግባር ላይ እንደሚሳተፉም ተናግረዋል፡፡
ችግሩ መፍትሄ እንዳያገኝ ያደረገው በክልሉ ጉዳዩ የሚመለከተው ተቋም አለመዋቀሩ እና በተዋረድ የተዘረጉ አሰራሮች አለመኖራቸው ነው ብለዋል፡፡ በዚህም ቢሮው ብዙ ርቀት ተጉዞ መስራት እንዳልቻለ አመላክተዋል፡፡
አሁንም ድረስ በርካታ የማህበረሰብ ክፍሎች ወደ ቤቲንግ የውርርድ ቤቶች ማቅናታቸውን ተከትሎ ለከፋ የኢኮኖሚ ቀውስ እና የአእምሮ ጤና እየተጋለጡ ነው ተብሏል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ