ኅዳር 24 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ የመሬት ይዞታ ማረጋገጥና ምዝገባ ላይ በዲጅታልና በወረቀት ሆኖ በሚቀርብበት ወቅት የሚፈጠሩ ቅሬታዎችና ክፍተቶች ካሉ በወረቅት ያለው ህጋዊ እንደሚሆን በከተማ መሠረተ ልማት ሚኒስቴር የመሬትና ካዳስተር ሃላፊ አቶ ብዙአለም አድማሱ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አዲሱን አዋጅ ባቀረቡበት ወቅት ተናግረዋል፡፡
የመሬት ይዞታ ማረጋገጥና ምዝገባ ላይ የተፈጠሩ አለመግባባቶች፤ ቅሬታዎች እና ክሶች ካጋጠሙ በወረቀት ያለው ማስረጃ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ መሃተም ከያዘ ህጋዊ ሆኖ እንደሚቀርብ ጠቁመዋል፡፡
የይዞታ ማረጋገጥ የምዝገባ ስራ ላይ ከዚህ ቀደም ከፍተኛ ክፍተቶች እንደነበሩ የሚናገሩት ሃላፊው፤ በተለይም በዜጎች የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ይስተዋሉ የነበሩ ክፍተቶችን በተሻሻለው አዋጅ መቅረፍ እንደሚቻል ገልፀዋል፡፡
ከተሞች ከመሬቶቻቸው መጠቀም የሚችሉበትን አካሄድም አዋጁ መያዙን አንሰተው በፍርድ ቤት ይዞታቸው ሳይረጋገጡ የሚቆዩ መሬቶች ቶሎ ምላሽ እንዲሰጣቸው ማስቻልንም እንደሚያካትት ጠቁመዋል፡፡
በነባሩ ሕግ ያጋጠሙ የሕግ ክፍተቶችን ለማስተካከልና ሌሎች የሊዝ ሥርዓቱን ይበልጥ ዉጤታማ የሚያደርጉ ድንጋጌዎችን ማካተት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤ እንዲሁም ሀገሪቱ ከደረሰችበትና ልትደርስበት የምትፈልገዉን የዕድገት ደረጃ ባገናዘበ መልኩ አዋጁ መሻሻሉን በከተማ መሠረተ ልማት ሚኒስቴር የመሬትና ካዳስተር ሃላፊ አቶ ብዙአለም አድማሱ ተናግረዋል፡፡
ትላንት ህዳር 23 ቀን 2017 ዓ.ም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ መሰረተ ልማት እና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ አዋጅ እንዲሁም የከተማ መሬትን በሊዝ ስለመያዝ ባወጣው ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ይፋዊ የህዝብ ውይይት ተካሂዷል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ