ኅዳር 23 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ጉባኤው በመቄዶንያ በጎ አድራጎት ማህበር የፀሎት መርኃ ግብር ባከናወነበት ወቅት ነው ይህን ያለው። በመርኃ ግብሩ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ፀሐፊ፤ የሃይማኖት ተቋማት መሪዎችና የሃይማኖት አባቶች ተሳትፈዋል።
የጉባኤው ጠቅላይ ፀሐፊ ቀሲስ ታጋይ ታደለ፥ ሰላም የመግባባት፤ የመተማመን እና በነጻነት የመንቀሳቀስ መሰረት መሆኑን ገልጸዋል።
ሰላም ለሰው ልጅ ሁሉ አስፈላጊ መሆኑን የተናገሩት ጠቅላይ ጸሐፊው፤ ሁሉም ከጥላቻ፣ ከቂም፣ ከጦርነትና ከበቀል መራቅ እንዳለበት አሳስበዋል። ሰላም ከሌለ ተስፋ አይኖርም ያሉት ቀሲስ ታጋይ፤ ተስፋ፣ ዕድገትና ብልፅግናን ለማረጋገጥ በቀዳሚነት ሰላም ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
በሀገራችን ሰላም ሰፍኖ የሚጠበቀው አንድነትና ዕድገት እንዲመጣ ሁላችንም የድርሻችንን ልንወጣ ይገባልም ሲሉ አክለዋል። ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዘርና ሀይማኖት ሳይገድበው በአንድነት ለሰላም መቆም እንደሚገባውም በአፅንዖት ተናግረዋል።
የመቄዶንያ በጎ አድራጎት ማህበር መስራች ቢንያም በለጠ በበኩላቸው፥ ማዕከሉ በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች በሚገኙ 44 ቅርንጫፎቹ ከ8 ሺህ በላይ አረጋዊያንና የአዕምሮ ህሙማንን እየረዳ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።
በቀጣይም ቅርንጫፎቹን ወደ 240 ለማድረስ እየሰራ እንደሚገኝም ተናግረዋል። መቄዶንያ ማለት ትንሿ ኢትዮጵያ ነች ያሉት አቶ ቢኒያም፥ የሀይማኖት፣ የዘር፣ የቀለም ልዩነት ሳይኖር ሁሉም የሚደገፉበት እንደሆነ አብራርተዋል።
የኢትዮጵያ ሀይማኖት ተቋማት ፕሮግራሙን በማዘጋጀትና የማዕከሉን የስራ እንቅስቃሴ በመጎብኘቱም ምስጋናቸውን አቅርበዋል። መቄዶንያን ለመረዳት በሚደረገው ተግባር ውስጥ ሁሉም እንዲሳተፍም ጠይቀዋል፡፡
የእምነት አባቶቹ ለሃገር ሰላምና መረጋጋት ለመፀለይና በተለያዩ ምክንያቶች ችግር ውስጥ ከወደቁ ወገኖች ጎን መሆናችንን ለማሳየት በመቄዶንያ በጎ አድራጎት ማህበር የጸሎት መርኃ ግብር እንዳከናወኑ ገልጸዋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ