ኅዳር 23 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በምዕራብ ጎንደር መተማ ወረዳ መቃ ቀበሌ ከሚንቀሳቀሱ የታጣቂ ተወካዮች ጋር ውይይት መካሄዱ ተገለጸ፡፡ በውይይቱ በመቃ ቀጠና የሚንቀሳቀሰው ራሱን “የቅማንት ታጣቂ ቡድን” ብሎ የሚጠራው ኀይል በሀገር ሽማግሌዎች አገናኝነት በተደረገው ውይይት የመንግሥትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው በሰላማዊ መንገድ በምህረት ለመግባት መስማማታቸው ተገልጿል፡፡
ታጣቂዎቹ ከሕዝባቸው ጋር በመቀላቀል ከሀገር ሽማግሌዎች፣ ከቀበሌያቸው መሪዎች እና ከመንግሥት አካላት ጋር አብረው ለመሥራት ስምምነት ላይ መድረሳቸው ነው የተገለጸው።
በቀጣይም በስራቸው ያሉ እስከ 250 የሚደርሱ አባሎቻቸውን ይዘው መንግሥት በሚሰጣቸው አቅጣጫ መሠረት የተሃድሶ ሥልጠና ወስደው ወደ ቀደመ ሕይዎታቸው እንደሚመለሱም መግባባት ላይ ተደርሷል ተብሏል፡፡
የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እና የአካባቢው ማኅበረሰብ ወደ ሰላም የተመለሱ ታጣቂዎችን በመንግሥት በኩል እንዲቋቋሙ የሚደረገውን ጥረት በልዩ ልዩ መንገድ ለመደገፍ እንደሚሠሩም ተመላክቷል ሲል በአማራ ክልል የብልጽግና ፖርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ