ኅዳር 21 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የብልፅግና ፓርቲ ባለፉት አምስት አመታት ከጎረቤት ሃገራት ጋር ከቃላት መወራወር ባለፈ ግጭት ውስጥ እንዳልገባ ተናግረዋል፡፡
ብልጽግና ፓርቲ አምስተኛ የምስረታ ክብረ በዓሉን ባከበረበት ወቅት ባደረጉት ንግግር የኢህአዴግ መንግስት ወደ ስልጣን በመጣባቸው አምስትና ስድስት አመታት ከበርካታ ጎረቤት ሀገራት ጋር ወደ ግጭት ውስጥ መግባቱን ተናግረዋል፡፡
የብልፅግና መንግስት ግን በአንጻሩ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ከቃላት ባለፈ ወደ ግጭት እንዳልገባም ተናግረዋል፡፡
ለውጡ ከመጣ በኋላ ከሁሉም ጋር በሰላምና በትብብር መንግስታቸው እንደሚሰራ በማመላከት በተለይ ደግሞ ከጎረቤት ሀገራት ጋር በትብብር እንደሚሰሩ አክለዋል፡፡ አሁን ላይም የውጭ ዲፕሎማሲ ፖሊሲያቸው ፍሬ ማፍራቱን አስረድተዋል፡፡
የኢህአዴግ መንግስት ከሁሉም ጎረቤት ሀገራት ጋር ተዋግቷል ማለት በሚቻል ደረጃ ግጭት ውስጥ ገብቷል ያሉ ሲሆን ፤ ለአብነትም በ1983 መጨረሻና በ198 መጀመሪያ አመታት በጋምቤላ ክልል በኢታንግ አካባቢ ከደቡብ ሱዳን ጋር በወቅቱ የደርግ ወዳጅ ተደርጎ ይወሰድ የነበረውን ደቡብ ሱዳንን እንደጠላት ፤ ሰሜን ሱዳንን ደግሞ እንደ ወዳጅ በመመለከት ሁለቱ አካላት ወደ ግጭት ሲገቡ ሰሜን ሱዳንን በመደገፍ በአሶሳ ፤ በመተማ ፤ በኤርትራና በዩጋንዳ ሰፊ ግዛት በማካለል ተዋግተናል ብለዋል፡፡
ትንሽ ቆይቶ ከኤርትራ ፤ ከሱማሊያ ጋር ወደ ግጭት መግባቱን ተናግረዋል፡፡
በወቅቱ የኦነግ ጦር ካምፕን ለመምታት ሲባል ከኬኒያ ጋርም ወደ ግጭት ተገብቶ እንደነበረ በማስረዳት ፓርቲያቸው ብልጽግና ባለፉት አምስት አመታት ከቃላት መወራወር ባለፈ ከአንድም ጎረቤት ሀገር ጋር ወደ ግጭት አለመግባቱን ተናግረዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ