ኅዳር 21 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ብልፅግና ፓርቲ ባለፉት አምስት አመታት ያሳካቸው ድሎች በሁለት እጃችን አፍሰን አንጨርሰውም ሲሉ ፓርቲዊ አምስተኛ የምስረታ በዓሉን በአከበረበት ወቅት ተናግረዋል።
ይህ ማለት ከተግዳሮት የፀዱ አምስት አመታት ነበር ማለት እንዳልሆነም አስገንዝበዋል።
አምስት አመት ማለት በአንድ እጅ በጣት የሚቆጠር ጊዜ ማለት ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጊዜው አጭር መሆኑ ሳይሆን ቀን ከሌት በመስራት ያመጣናቸው ስኬቶች አስደማሚ ናቸው ብለዋል።
ፓርቲያቸው ከዲሞክራሲ አንፃር ሲቪክ ማህበራት መስፋት አለባቸው ብሎ ስለሚያምን እድገታቸው በመቶኛ ከ1መቶ በላይ ፣ ሚዲያዎችም በተመሳሳይ እድገታቸው ባለፉት አመታት በመቶኛ ከመቶ በላይ መሆኑን ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ተዋጊ አውሮፕላን ፀሀይ ሁለትና ዲሮኖችን መገጣጣም የቻለችው በዚሁ አምስት የብልፅግና የስኬት አመታት መሆኑን አክለዋል።
በተጨማሪም ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ሳትላይት ወደ ሕዋ ያመጠቀችበት በአፍሪካ ትልቁን የጥራት መንደር ፣ በአመት ከአንድ መቶ ሚሊዮን መንገደኞችን ማስተናገድ የሚችል የአውሮፕላን መረፍያን ማስፋፊያ ፣ ኢትዮጵያ አመታዊ በጀቷ ከአንድ ትሪሊዮን የተሻገርበት አምስት አመታት አንደነበር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በንግግራቸው አምላክተዋል።
ከኢኮኖሚ ረገድም ከፍተኛ የእዳ ሽግሽግ የተደረገበት መንግስታቸው ወደ ኃላፊነት ሲመጣ አመታዊ የሀገሪቷ እዳ ከአመታዊ ጥቅል ምርቷ 59 በመቶ ያህል እንደነበርና ከዚህም ውስጥ 30 በመቶ ያህሉ የውጭ እዳ መሆኑን ተናግረዋል።
ይህ እዳ ዛሬ ላይ 13 በመቶ ዝቅ ከማለቱም በላይ በሚቀጥሉት ሁለትና ሶስት አመታት የኢትዮጵያን እዳ ከአስር በመቶ በታች ዝቅ ለማድረግ መንግስታቸው እንደሚሰራ አፅንዖት ሰጥተዋል።
እነዚህ ሁሉ ስኬቶች ከትግዳሮት በፀዳ መልኩ እንዳልመጣም አስገንዝበዋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ