ኅዳር 20 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በሃገራችን የኮንዶም አቅርቦት እጥረት መኖሩን ተከትሎ የኤች አይ ቪ ኤድስ ስርጭት እየጨመረ እንዳለ ይገለጻል።
የኤች አይ ቪ ኤድስ ስርጭትን ለመከላከል የሚረዳው ኮንዶም ወደ ሃገር ውስጥ ሲገባ ታክስ እንደሚጣልበትም የሚታወቅ ነው።
ቀደም ባሉት ጊዜያት ኮንዶም ወደ ሃገር የሚገባው መንግስት ከግሎባል ፈንድ በሚያገኘው እርዳታ በጤና ተቋማት የሚከፋፈል እና በአነስተኛ ዋጋ ወደ ሃገር በሚያስገቡ የስነ ተዋልዶ ተቋማት በመሆኑ ተደራሽነቱ ላይ ከፍተኛ ክፍተት እንዲኖር አድርጎታል ሲሉ ባለሙያዎች ይገልጻሉ።
ይህን ችግር ለመቅረፍ ጤና ሚኒስቴር ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ታክሱ እንዲነሳ መደረጉ ተገልጿል።
በገንዘብ ሚኒስቴር የህግ መምሪያ እና ህግ ጉዳዮች አማካሪ አቶ አብረሃም ረጋ ከዚህ ቀደም በነበረው አሰራር ምርቱን 35 በመቶ የታክስ ክፍያ ተከፋፍሎ እንዲገባ የሚስያገድድ ፖሊሲ እንደነበር አስታውሰው፤ ከባለፈው ሰኔ 13 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ የመመሪያ ማሻሻያ በማድረግ የታክስ ክፍያ እንዲነሳ መደረጉን አስታውቀዋል።
የታክስ ክፍያው ከፍተኛ በመሆኑ ዋጋው የተጋነነ እንዲሆን አድርጎታል፤ በዚህም ምርቱ በበቂ ሁኔታ ለህብረተሰቡ ተደራሽ እንደማይሆን ነው የገለጹት።
የመመሪያ ማሻሻያው የኤች አይ ቪ ኤድስ ተጋላጭነት ባለባቸው አከባቢዎች ምርቱ በአነስተኛ ዋጋ ተደራሽ እንዲሆን ያግዛል ሲሉ ገልጸዋል።
ቀደም ሲል የተነሳውን ሃሳብ የሚያጠናክሩት በኤ.ኤቼ.ፍ ኢትዮጵያ የኤች አይ ቪ መከላከልና ምርመራ አገልግሎት ግንዛቤ ፕሮግራም ሃላፊ አቶ ቶሎሳ ኦላና የታክስ ክፍያው ከፍተኛ እንደነበር ገልጸዋል። የመመሪያው መሻሻል የግሉ ባለሀብቶች በዘርፉ እንዲሰማሩ እንደሚያደርግ እንዲሁም የኤች አይ ቪ ኤድስ ስርጭትንም ለመከላከል እንደሚያግዝ ተናግረዋል፡፡
የገንዘብ ሚኒስቴር የህግ መምሪያ እና ህግ ጉዳዮች አማካሪው አቶ አብረሃም ባለሀብቶች መንግስት ያመቻቸውን መልካም አጋጣሚ በመጠቀም በዘርፉ እንዲሰማሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ