ኅዳር 20 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአውስትራሊያ ጨካኙ ሰው የሚል ቅጽል የተሰጠው ግለሰብ የቀድሞ የሕጻናት እንክብካቤ ሠራተኛ በነበረበት ጊዜ ወደ 70 በሚጠጉ ልጃገረዶች ላይ አስገድዶ መድፈርን ጨምሮ የተለያዩ ጾታዊ ጥቃቶችን በመፈጸሙ ነው የዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት የተፈረደበት።
የ47 አመቱ አሽሊ ፖል ግሪፊዝ እ.ኤ.አ.ከ2003 እስከ 2022 ባለው ጊዜ ውስጥ በአውስትራሊያ ኩዊንስላንድ ግዛት በአንድ የህፃናት ማቆያ ማእከል ውስጥ የፈጸማቸውን 307 ወንጀሎችን አምኗል።
ዳኛው ፖል ስሚዝ የወንጀሎቹን አይነት እና መጠን አስነዋሪ፤ እጅግም አሳፋሪ፤ ለማመንም የሚከብዱ ናቸው ሲሉ ገልጸውታል።
ከዚህኛው ክስ በተጨማሪ ወንጀለኛው በአገሪቱ ኒው ሳውዝ ዌልስ ግዛት እና በጣሊያን ከ20 በላይ የሚሆኑ ህጻናትን በማንገላታት ክስ እንደተመሰረተበት ቢቢሲ ጠቅሷል።
ግሪፍት ለመጀመሪያ ጊዜ እ.ኤ.አ በነሐሴ ወር 2022 በአውስትራሊያ የፌደራል ፖሊስ መያዙን እና ከተያዘ ከአንድ አመት በኋላ ከ1ሺ 600 በላይ በሚሆን የወሲብ ወንጀል ተከሷል።
መርማሪዎች ግለሰቡ ራሱ ቀርጾ ያስቀመጣቸውን ወንጀሉን የሚያጋልጡ በሺዎች የሚቆጠሩ ፎቶግራፎች እና ተንቀሳቃሽ ምስሎችን አግኝተዋል።
በ28 የአስገድዶ መድፈር ክሶች፣ ወደ 200 የሚጠጉ ክሶች ደግሞ በህፃናት ላይ ተገቢ ያልሆነ አያያዝ እንዲሁም በርካታ የህፃናት ጉልበት ብዝበዛን የሚያበረታቱ ፅሁፎችን የመጻፍ እና ማጋራት ክሶችን አምኗል ተብሏል።
ፍርድ ቤቱም የእድሜ ልክ ጽኑ እስራት እንደፈረደበት ያስታወቀው የቢቢሲ ዘገባ ነው፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ